የፓሪስ ኦሎምፒክ ኮከብ ጋቢ ቶማስ በአዲስ አበባ ልትገባ ነው

Date:


በአለም አትሌቲክስ አውድ ውስጥ ደማቅ ስም ያላት አሜሪካዊቷ የ200 ሜትር የኦሎምፒክ ሻምፒዮን ጋቢ ቶማስ፣ በኢትዮጵያ በሚካሄደው ታሪካዊ የግራንድ ፕሪክስ ውድድር ላይ እንደምትሳተፍ አረጋገጠች።


ታሪካዊ ውድድር በአዲስ አበባ


ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምታስተናግደው የአንድ ቀን ዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ (World Athletics Continental Tour) ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ይህ ውድድር የአለም የጥቁር ህዝቦች ኩራት በሆነችው አዲስ አበባ መካሄዱ ልዩ ትርጉም የሚሰጠው ሲሆን፣ የጋቢ ቶማስ መገኘት ደግሞ ውድድሩን በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል።


የጋቢ ቶማስ ድንቅ ስኬቶች
ጋቢ ቶማስ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች በአጭሩ፦
በ200 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት።


በዚሁ ኦሎምፒክ በ4×100 ሜትር እና በ4×400 ሜትር የሪሌ ውድድሮች ከአጋሮቿ ጋር ተጨማሪ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለአሜሪካ አስገኝታለች።


በቡዳፔስት ዓለም ሻምፒዮና የብር እንዲሁም በቶኪዮ ኦሎምፒክ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ናት።


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (ኢአፌ) እንደገለጸው፣ የዚህች አንጋፋ አትሌት መምጣት ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገትና ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...