ዮድ አቢሲኒያ በከተማ አስተዳደሩ በተሰጠው ቦታ አዲስ ቅርንጫፍ ከፈተ

Date:

አዲሱ ቅርጫፍ የት ይገኛል ?

አዲሱ ቅርጫፍ ቴዎድሮስ አደባባይ ፊት ለፊት ይገኛል ፤ ቅዳሜ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የድርጅቱ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ ቀኝ አዝማች ትዕዛዙ ኮሬ ትናንት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ይህን ቦታ እንዴት ሊያገኙ ቻሉ ?

ዮድ አቢሲንያ የኢትዮጵያን ባህል፤ ቱሪዝም፤ ሃገራዊ መለያ በማስጠበቅ እና ማህበራዊ ግዴታን በመወጣት ላበረከትው አስተዋጽዖ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር በቴዎድሮስ አደባባይ ባስገነባው እና በሚመራው ህንጻ ላይ አዲስ ቅርንጫፉን ከፍቶ አገልግሎት እንዲሰጥ ዕድል በመስጠቱ እንደሆነ ተገልጿል።

እውቅና

ዮድ አቢሲኒያ ጠቅላላ ንግድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለፉት 22 ዓመታት የሃገራችን ኢትዮጵያን ”ባህል ፤ ታሪክ ፤ ቅርሶች እንጠብቅ፤ እናክብር ፤ ቋንቋችንን እናሳድግ ” በሚል መርዕህ ለተለያዩ ጉዳዮች ከመላው ዓለም ወደ ሃገራችን ለመጡ የኢትዮጵያ እንግዶች የተለያዩ አገልግሎቶችን ሲሰጥ በመቆየቱ ላበረከተው በጎ ተግባርና ሀገርን ለአለም የማስተዋወቅ ስራ ”የኢትዮጵያ የባህል እና የቱሪዘም አምበሳደር” የሚል ዕውቅና ተሰጥቶታል፡፡

በአዲሱ ቅርጫፍ የሚሰጠው አገልግሎት

👉 የባህል ምግብና መጠጦች
👉 የብሔር ብሄረሰቦችን ሙዚቃዎችና ውዝዋዜዎች
👉 የሰርግ
👉 የመልስ እና መሰል ሁነቶች
👉 ዘመናዊ ባር እና ሬስቶራንት
👉 የካፌ አገልግሎት እና ሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶች ይገኙበታል ብለዋል፡፡

የፈጀው ወጪ

ከግንባታው ውጪ የፕሮጀክቱን ግንባታ ለማሟላት 150 ሚሊየን ብር መውጣቱን የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘሪሁን ክብረት ተናግረዋል።

የሥራ እድል ፈጠራ

በአዲሱ ቅርንጫፉ ብቻ ለ250 ሰዎች የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል።

በጎ አድራጎት

ድርጅቱ ከበርካታ በጎ አድራጎት ድረጅቶች ጋር መቄዶንያ የአረጋዊያን መረዳጃ ፣ ሜሪጆይ ጨምሮ ከሌሎች ጋር በመስራት ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ያለ ተቋም መሆኑ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...