ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ዓለም የሚፈልጋቸው ማዕድናት ያሉበት አካባቢ ነው

Date:

በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ያሉ አካባቢዎች አሁን ዓለም የሚፈልጋቸው ዋና ዋና ማዕድናት ያሉበት አካባቢ መሆኑን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የማዕድን ሚኒስቴርን የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡

የማዕድን  ሚኒስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ እንደገለጹት፤ በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ያሉ አካባቢዎች አሁን ዓለም የሚፈልጋቸው ዋና ዋና ማዕድናት ያሉበት አካባቢ ነው፡፡

የአገሪቱ አንደኛ ደረጃ የሚባሉ ማዕድናትን ፍለጋ ላይ እየተሰራ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ በጉጂ፣ ቦረና፣ ከፊል ሶማሌ፣ ሱማሊያና ኬንያ ድንበር እና ሰቆጣ አካባቢ ያለው የብረት ክምችት ጥናት እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ አካባቢዎቹ ሊቲየም፣ ታንታለም፣ ኒኬል፣ ማንጋኒዝ የሚባሉ ዋና ዋና ማዕድናት ያሉበት ነው፡፡

በውስን አቅም ቢሆንም በእነዚህ አካባቢዎች ላይ የምርመራ ሥራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ የአገር ፍላጎትን መሰረት በማድረግ በቅደም ተከተል በመሰራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጋዜጣ ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...