የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስር በሰደደ የደምስር ህመም መጠቃታቸውን የነጩ ቤተመንግስት አስታወቀ።
ዶናልድ ትራምፕ እጅ ላይ መቁሰል የሚያሳዩ ምስሎች ተከትሎ አያሌ መላምቶች ሲወጡ ቆይተዋል፤
በስተመጨረሻም የነጩ ቤተመንግስት በፕሬስ ሴክሬታሪያት ሀላፊዋ ካሮሊን ሌቪት አማካኝነት ትራምፕ ስለገጠማቸው ህመም አብራርተዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እግራቸው ላይ የተከሰተውን እብጠት ተከትሎ የደም ቧንቧ ጨምሮ አጠቃላይ ምርመራ ስለማድረጋቸው በመግለጫው አስታውቀዋል።
ፕሬስ ሴክሬታሪዋ አክለውም ትራምፕ የገጠማቸው በእጃቸው ላይ ደምስር መበጣጠስ ችግር ሲሆን እጅ ላይ በሚደርስ ተደጋጋሚ ጫና አማካኝነት እንደተከሰተባቸው ነገርግን ህመማቸው ለከፉ ጉዳት የሚዳርግ እንዳልሆነ አንስተዋል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው በአሜሪካ ታሪክ ብቅ ካሉ ጤነኛ መሪዎች አንዱ እያሉ በተደጋጋሚ እራሳቸውን ሲጠሩ ይስተዋላል።
BBC
