ዶይቸ ቨለ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ላይ የቀረበበትን ክስ ተቃወመ

Date:

ዶይቸ ቨለ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ቦን ከተማ የሚገኙትን የአማርኛው ሬዲዮ ጣቢያ ጋዜጠኞችን ጭምር በደፈናው ወንጅሏል ሲል አዲስ ባወጣው መግለጫ ተቃውሞውን ገለጸ።

ባለሥልጣኑ፣ በቦን የሚገኙ ሠራተኞቹ ላይ “የተሳሳተ” እና “ሁከት” ሊቀሰቅስ ወይም “ሰላም” እና “ጸጥታ” ሊያናጋ የሚችል መረጃ ያሰራጫሉ የሚል ክስ ማቅረቡን ጣቢያው አመልክቷል።

የአማራ እና ትግራይ ክልሎች ዘጋቢዎቹ በዘላቂነት መታገዳቸውን የተቃወመው ጣቢያው፣ ባለሥልጣኑ ለእገዳው “ተጨባጭ ምክንያት” አላቀረበም በማለት ወቅሷል። ዶይቸ ቨለ የባለሥልጣኑን ክሶች ውድቅ በማድረግ ከዘጋቢዎቹና ቦን ከሚገኙ ሠራተኞቹ ጎን እንደሚቆም አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...