ጆ ባይደን  የፕሮስቴት ካንሰር እንዳለባቸው በህክምና ታወቀ

Date:



የ82 አመቱ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በፕሮስቴት ካንሰር መጠቃታቸውን ወደ አጥንታቸውም መዛመቱን ፅህፈት ቤታቸው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። በጥር ወር ከስልጣን የወረዱት ባይደን ባለፈው ሳምንት የሽንት ምልክቶች ከታዩ በኋላ አርብ እለት በበሽታው መጠቃታቸው ታውቋል።

የተጠቁበት ካንሰር በከፍተኛ ደረጃ የሚመደብ እና የካንሰር ህዋሶች በፍጥነት ሊሰራጭ ይችላል ሲል ካንሰር ሪሰርች ዩናይትድ ኪንግደም አስታውቋል። ባይደን እና ቤተሰባቸው የህክምና አማራጮችን እየገመገሙ ይገኛል ተብሏል። ፅህፈት ቤቱ አክሎም ካንሰሩ ሊታከም የሚችል ነው ብሏል ።

ስለ ምርመራው ዜና ከተሰማ በኋላ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከሁሉም ወገኖች ድጋፍ አግኝተዋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የግል ንብረታቸው በሆነው የማህበራዊ ሚዲያ ትሩዝ ሶሻል ላይ እንደፃፉት እኔ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ “ስለ ጆ ባይደን የቅርብ ጊዜ የህክምና ምርመራ ስንሰማ ሀዘኔታ ተሰምቶናል” ብለዋል።የቀድሞዋን ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደንን በመጥቀስ መልካም ምኞታችንን ለጂል እና ለቤተሰቦቻቸው እናቀርባለን።”ለጆ ባይደን ፈጣን እና ስኬታማ ማገገም እንመኛለን።” ሲሉ ትራምፕ አክለዋል።


በባይደን አስተዳደር ስር ያገለገሉት የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ እና ባለቤታቸው ዳግ ኤምሆፍ የባይደንን ቤተሰብ በጸሎታቸው እያሰቡ መሆናቸውን በኤክስ ላይ ጽፈዋል።

ከ2009 እስከ 2017 በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉት ባራክ ኦባማ  ጆ ባይደን ምክትላቸው የነበሩ ሲሆን በኤክስ ላይ በፃፉት መልዕክት እኔ እና ባለቤቴ ሚሼል “ስለ መላው የባይደን ቤተሰብ እያሰብን ነው” ብለዋል። ኦባማ እንዳሉት “ለካንሰር በሁሉም መልኩ ፈጣን ሕክምናዎችን ለማግኘት ከጆ ባይደን የበለጠ ማንም አልሰራም፣ እናም ይህን ተግዳሮት እንደሚታገሉት እርግጠኛ ነኝ።

ፈጣን እና ሙሉ ፈውስ እንዲያገኙ እንጸልያለን” ብለዋል። እ.ኤ.አ. በ2016፣ ኦባማ ለባይደን የካንሰር የመንግስት አቀፍ የምርምር ፕሮግራም እንዲመራ ኃላፊነት እንደሰጧቸው ይታወሳል። የፕሮስቴት ካንሰር በወንዶች ላይ በጣም የተለመደ ካንሰር ሲሆን ከቆዳ ካንሰር ቀጥሎ ይቀመጣል። የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (ሲዲሲ) ከ100 ወንዶች 13 ቱ በሕይወታቸው ውስጥ በሆነ ወቅት የፕሮስቴት ካንሰር ይያዛሉ ብሏል። እድሜ ደግሞ የበሽታውን ተጋላጭነት ይጨምራል ሲል ሲዲሲ አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...