በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ለኢትዮ ፌሪስ ጣና የሀገር ውስጥ የውሃ ትራንስፖርት እንዲያገለግሉ ከተገዙት ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች መካከል ሁለተኛዋ ጣናነሽ-2 ጀልባ በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ ገብታለች፡፡
ከዚህ ቀደም ከጂቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ የጀመረችው የጣናነሽ-2 ጀልባ ለአንድ ወር ተኩል ያህል ተጉዛ በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያን ድንበር ማቋረጧ ነው የተነገረው።
በጉዞ ወቅት ያጋጠመውን አስቸጋሪ የመንገድ ሁኔታ ለመፍታት የተለያዩ የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የመንግሥት አካላት ከፍተኛ ርብርብ ማግረጋቸው ተገልጿል፡፡
በዚህም የጣናነሽ-2 ጀልባ ከሰዓታት በፊት የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጣ ደወሌ መግባቷን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡
ጣናነሽ 2 ዘመናዊ የሰው ማጓጓዣ እና የመዝናኛ ጀልባ ስትሆን 38 ሜትር እርዝመት ያላት ሲሆን፤ በአንድ ግዜ 188 ሰዎችን የመጫን አቅም እንዳላትም ተነግሯል፡፡
