ባርሴሎና ሁለት ጨዋታዎች እየቀሩት የ2024/25 የስፔን ላሊጋ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።
በ36ኛ ሳምንት የላሊጋ መርሐ ግብር ባርሴሎና ኤስፓኞልን ከሜዳው ውጭ 2 ለ 0 አሸንፏል።
ጎቦቹን ለሚን ያማል እና ፌርሚን ሎፔዝ አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ባርሴሎና የዋንጫው ባለቤት ሆኗል።
በዘንድሮው ውድድር አመት በስፔን ላሊጋ በአማካይ እድሜ ትንሹ (25) የሆነውን ቡድን ይዞ የቀረበው ባርሳ በሀንስ ፍሊክ ስር ድልን እያጣጣመ ነው ።
የስፔን ኮፓ ዴልሬይን እና ላሊጋውን ማንሳታቸውን አረጋግጠዋል ።
ላሊጋው 1928እኤአ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ ማድሪድ 36 ጊዜ በማንሳት ቀዳሚው መሆን ባርሳ በ28 ይከተላል ።
