ጦርነት ያደናቀፈው ጉዞ አድዋና ያሬድ ሹመቴ‼️

Date:

የኢትዮጵያው ሰው Yared Shumete – ያሬድ ሹመቴ ባለ ብዙ ታሪክ ነው ። ጎልማሳው ያሬድ የሥነ-ጽሁፍ ባለሙያ ፣ ገጣሚ ፣ የሙዚቃ ዜማ ደራሲ ፣ የእምዬ ምኒሊክ የትውልዴ ማስታወሻ የጉዞ አድዋ ፊታውራሪ ፣ የፊልም ባለሙያ ፣ ትጉህ ሰብአዊ ድጋፍ አስተባባሪ ነው ። ያሬድ መልኩ ዥጉርጉር ልበ ቀና ሃገር ወዳድ ነው ።

ከ Dawit Tesfaye ጋር በ Dejaf TV ሦስተኛ ክፍል ወግ ያሬድ ሹመቴ በዘመነ ወያን ወደ አቶ መለስ ዜና ከጥበብ ሰዎች ጋር ካደረጉት ውይይት ጀርባ ስለነበረው ተሳትፎውና ደረቅ እውነት ይነግሮናል ።

ጉዞ አድዋ ስለተመሰረተበት አቦይ ስብሃት ስለደገፉት ድንቅ ጉዞና ለጊዜው ስለከሸፈው መንገድ አስደማሚ ሂደቱን ያጫውተናል ። በጉዞ አድዋ አንጎለላ ላይ ጉዞ አድዋ ጉዞ ላይ በተለያየ አመት የአድዋን ጉዞ ተቀላቅለው አድዋ ስለተጓዙት ሁለት ውሾች ገራሚ ታሪክ ያጫውተናል ።

ያሬድ የመጨረሻውን የጉዞ አድዋ ጉዞ ሲያደርጉ አድዋ ላይ በተደረገው ትዕይንት በተሰጣቸው ደቀቂዎች ተጓዦች ፕሬዚ ሳህለ ወርቅ ባሉበት መድረክ የእምዪ ምኒሊክን ስም ከፍ አድርገው ዘምረው ምጣታቸውን ሲጫዎት ስሜታዊ ያደርጋል።

መልከ ብዙ በእኛ ሃገር ስለ ሃገር የሚሰሩ ስራዎች ድጋፍ ማድረግ ስለንነፍግበት ርክሰታችን እውነቱን ሲያጫውተን በጉዞ አድዋ ማትረፍ ቀርቶ መክሰሩ እንጀማያስከፋው ሲናገር ውስጤ ታሟል ።

ከወያኔ ጋር በነበረው ጦርነት ወቅት ያሬድ ገለልተኛ ሆኖ ብዙዎች “መከላከያ ተደፈረ ” ብለን ጠንካራ አቋም ይዘን ተገናኝተን ተወያይተናል ። ዛሬ ሁሉም አልፎ ያሬድ የያዘው አቋም ትክክል ስለመሆኑ አስታውሸ ራሴን የወቀስኩ ዛሬ ነው ።

ያሬድ በጉዞ አድዋ የዛሬን የኢትዮጵያ መልዕክት ፣ የዛሬን ሰላም ማጣት ቀድሞ ማየቱን በጣፋጭ ወጉ አሳምሮ ይነግረናል ። በዚህ ጭውውት ያሬድ ካነሳቸው ወጎች መካከል “የካድሬ ሰዓት ” “አዲሱ አመት የሰላምና ብልጽግና አመት ይሁንላችሁ” ማለት የሸሸንበትን እውነት ስለ ” ጎላ ጎ ” የብዕር ስሙ ውብ አድርጎ ያጫውተናል ።

በነገራችን ያሬድ ሹመቴ ልበ ርህሩህ ሰብአዊ ሰው ነው ። ባንድ ወቅት በዓለ ፋሲካ ደርሶ ለተቸገሩት አንድ ደሮ በፋሲካ ብሎ ለሰብአዊ ድጋፍ ጥሪ አደረገ።

እኔም አክባሪ ወዳጅነቴ ቤተሰቦቸን አስተባብሬ ተቀላቅየ አውቃለሁ ። አዎ በፋሲካ አንድ ደሮ የወገኖቸን ጥልቅ የማላውቀው ማጣት መጎሳቆል ፤ የርህሩት ወገኖቸን ደግነት ተመልክቸ በደስታና በመከራው መካከል ተንሰቅስቄ አልቅሻለሁ ። ያሬድ አስለቅሶኛል

ብቻ መልከ ዥጉርጉሩ ያሬድ ሹመቴ ለእኔ የዚህ ትውልድ አርአያ የሚሆን የኢትዮጵያዊነት ትጉህ ዜጋ ምልክት ነው ። ኢትዮጵያ ሰላም ለመሆኗ ማረጋገጫው ጉዞ አድዋ ወደ ቀደመ ተመልሶ ማየት ነውና ለዚያች ሩቅ የምትመስለኝ ያብቃን ‼️

ያሬዶ እንወድሃለን ፤ እናከብርሃለን

ነቢዩ ሲራክ
ታህሳስ 3 ቀን 2018 ዓም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...

የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር፤ ለወረራ የታለመ ማደናገሪያ? ሩሲያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ውጥረትን ለመቀነስ...