የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ በታሪክ እጅግ አስገራሚ የሚባል ስኬት በማስመዝገብ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።
በፑሽካሽ አሬና ከአርሰናል ጋር ያደረጉት የፍጻሜ ፍልሚያ እስከ ጭማሪ ሰዓት 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ቀጥሎ፣ በስተመጨረሻ ፒኤስጂ በመለያ ምት አሸናፊ በመሆን ዋንጫውን በድጋሚ ወደ ፓሪስ ወስዷል።
በጨዋታው ካይ ሀቨርትዝ ለአርሰናል ቀዳሚ ግብ ቢያስቆጥርም፣ ፒኤስጂዎች ተስፋ ሳይቆርጡ በኦስማን ዴምቤሌ የ65ኛው ደቂቃ የፍጹም ቅጣት ምት ግብ ወደ ጨዋታው ተመልሰዋል።
መደበኛ የጨዋታው ክፍለ ጊዜና ጭማሪው 30 ደቂቃ 1 ለ 1 ተጠናቆ ፒኤስጂ በመለያ ምት 4 ለ 3 አሸንፏል።
