ለልብ ሕሙማን የገቢ ማሰባሰቢያ 350 ሺህ ዶላር ተሰበሰበ

Date:

የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ (Heart to Heart Children’s Aid) በማርዮት ሆቴል ዋሽንግተን ዲሲ ባከናወነው የማጠቃለያ መርሐግብር 350 ሺህ ዶላር ማሰባሰቡን የድርጅቱ መሥራች አቶ ብርሃን ተድላ አስታውቀዋል።

ከዚህ ውስጥ በቀጥታ በባንክ ገቢ የተደረገ 110 ሺ ዶላር  ገቢ የተገኘ ሲሆን ቀሪው ቃል የተገባና በአጭር ጊዜያት የሚሰበሰብ መሆኑን አንስተዋል።

በተገኘው ገቢ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ በወረፋ ላይ ለሚገኙ 120 ሕጻናት የልብ ቀዶ ጥገና ሕክምና ይሰጣል ተብሏል።

በተጨማሪም ኤፕሪል 24 ከጣሊያን በሚመጡ ባለሙያዎች አማካኝነት ለተጨማሪ 50 ሕጻናት ሕክምና የሚሰጥ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በወራት ጊዜ ውስጥ የሕክምና ተጠቃሚዎች ቁጥር 170 ለማድረስ ታቅዷል።

ድርጅቱ በቀጣይ አንድ ዓመት ውስጥ በአራት የሀገሪቱ አካባቢዎች የልብ ቀዶ ጥገና ማእከላትን ለማቋቋም አቅዶ እየሰራ ይገኛል።

በመርሐግብሩ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ወጣት አዶናይ ብርሃነ፣ ወ/ሮ ሀና ክብሩና ባለቤታቸው ሳሚ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...