“ለመንገዴ” የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ተደረገ

Date:

“በውጭ አገራት የሚሰሩ ዜጎችን መብትና ደህንነት ያረጋግጣል” የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከዓለም የስራ ድርጅት ጋር በመተባባር በውጭ ሀገራት ስራ ለሚሰማሩ ዜጎች የሚያገለግል “ለመንገዴ” የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያን ይፋ አድርጓል።

የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ነቢሃ ሞሃመድ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የሞባይል መተግበሪያው በራስ አቅም የለማ ሲሆን፤ ዜጎች ስለሚሄዱበት ሃገር በቂ መረጃ እንዲኖራቸው የሚያስችል ነው፡፡

በተጨማሪም ዜጎች በመዳረሻ ሀገራት በሚኖራቸው ቆይታ ችግር ቢገጥማቸው ሪፖርት ለማድረግ እንደሚያስችላቸው ጠቅሰው፥ መብትና ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።

መተግበሪያው የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነትን በተመለከተ ለዜጎች በቂ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ መንግስት ህገ ወጥ ፍልሰትን በማስቀረትና ዜጎችን በውጪ ሀገራት የስራ ስምሪት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።

የዓለም የስራ ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኩምቡላ ንዳባ በበኩላቸው፥ መተግበሪያው ዜጎች በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የስራ እድል እንዲያገኙ ከማስቻሉም በላይ መብትና ደህንነታቸውን ያረጋግጣል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት የተመረቀው መተግበሪያው፤ በቴሌብር ላይ የሚገኝ ሲሆን በአማርኛ፣ አረብኛና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ፋና ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...