ለቅርስ ጥበቃና ምርምር የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም

Date:

የቅርስ ጥበቃና የምርምር ዘርፍ ውስጥ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም አስፈላጊ ነው አሉ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው፡፡

ባለሥልጣኑ “የኢትዮጵያ ቅርስ ምርምር በዲጂታል ዘመን” በሚል መሪ ሃሳብ 3ኛውን ዓመታዊ የኢትዮጵያ ቅርስ ምርምር ጉባዔ እያካሄደ ነው፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ በኢትዮጵያ የሚገኙ ቅርሶችን ምዝገባ የሚያሳልጥ ሀገራዊ የመረጃ ቋት ለምቶ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

የቅርስ ጥበቃና የምርምር ዘርፍ ውስጥ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው ÷ ባለስልጣኑ ዲጂታል አሰራርን እየተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ሀገሪቱ ከጀመረችው ‘ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030’ ስትራቴጂ ጋር በማጣጣም የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ከየካቲት 2025 ጀምሮ ትልቅ የዲጂታላይዜሽን ሥራ ጀምሯል ነው ያሉት።

ተቋሙ በ2027 ዓ.ም የተወሰኑ አገልግሎቶችን፤ በ2030 ደግሞ ከቅርስ ጋር የተያያዙ አጠቃላይ አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ለማድረግ አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

የሙዚዬም አገልግሎትን ዲጂታላይዝ በማድረግ በተሻለ ሁኔታ ለማስተዋወቅና የጎብኝዎችን እርካታ ለማሳደግ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ቅርሶችን ለመጠበቅ፣ ለማልማትና ለትውልድ ለማስተላለፍ የተጠበቀና የተደራጀ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በቤ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...