ለአፍሪካ ሕዝብ ጤና፣ ስኬት፣ ሰላም እና ብልጽግናን እመኛለሁ – ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን

Date:

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአፍሪካ ቀንን አስመልክተው ለአፍሪካ ሕዝብ እና መሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዚዳንቱ የዘንድሮ የአፍሪካ ቀን ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት ማብቃት እና ከተመድ ምሥረታ 80ኛ ዓመት፣ እንዲሁም ተመድ በቅኝ ግዛት ሥር ያሉ ሀገራት ነጻ እንዲሆኑ አዋጅ ያፀደቀበት 65ኛው ዓመት ጋር መገናኘቱ ታሪካዊ ያደርገዋል ብለዋል።

የናዚ መሸነፍ እና የቅኝ ግዛት ሥርዓት መወገድ የ20ኛው መቶ ክፍለ ወሳኝ ክስተቶች እንደነበሩ ያስታወሱት ፑቲን፣ ይህም ለሰው ልጅ ሁሉ ነጻ እና ሰላማዊ ኑሮ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።

የአፍሪካ ሀገራት ነጻነታቸውን ባስከበሩባቸው ያለፉት ስድስት አሥርተ ዓመታት የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አካል ሆነው ማኅበረዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስኬቶችን ማስመዝገባቸውንም ፕሬዚዳንቱ ጠቅሰዋል።

ፕሬዚዳንት ፑቲን በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ ውስጥ የተመሠረተው የባለ ብዙ ወገኖች ትብብር እንዲሁም በርካታ ቀጣናዊ ትብብሮች በአህጉሪቱ የፀጥታ እና መረጋጋት እንዲጠናከር አስተዋፅኦ አድርገዋል ብለዋል።

ሀገራቸው ከአፍሪካ ጋር የቆየውን የወዳጅነት ግንኙነት እንዲጠናከር እንደምትፈልግ ያወሱት ፑቲን፣ በ2019 እና በ2023 የተካሄዱት የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤዎች ሩሲያ እና አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም እንዲይዙ ማስቻላቸውን ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በመጨረሻም ለአፍሪካ ሕዝብ ጤና፣ ስኬት፣ ሰላም እና ብልጽግናን ተመኝተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...