በክሮሺያ ዛግሬብ በተደረገው ኮንቲኔንታል ቱር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ ።
በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የቦታውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፋለች።
አትሌት ጉዳፍ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 3:58.14 ወስዶባታል ።
አትሌት ብርቄ ኃየሎም በ3:59.19 ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ሳምራዊት ሙልጌታ ስድስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በወንዶች 5 ሺህ ሜትር አትሌት ቢኒያም መሀሪ በ13:03.57 ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀል።
