ላንሴት ሆስፒታል ለዘላቂ ታካሚዎች  የሆስፒስ ማዕከል አስመረቀ

Date:

ላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል በሀገራችን በአይነቱ ልዩ የሆነና ለማይድን ወይም ዘላቂ የሆነ ሕመም ላለባቸው ታካሚዎች የሚያገለግለውን፤ “ሆስፒስ” እየተባለ የሚጠራውን የአገልግሎት ማዕከሉ አስመርቋል።

“ሆስፒስ” በማይድን በሽታ ተይዘው የሕይወታቸውን ፍፃሜ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ ሰዎች የሚሰጥ የሕክምና አገልግሎት ሲሆን፤ በመሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ማቋረጥን በማከናወን የሚደረግ የእንክብካቤ አይነት ነው።

በዚህም መሠረት  ተመርቆ ሥራ የጀመረው የአገልግሎት ማዕከል፤ ከባድ ሕመሞች ላላቸው ሕመምተኞች ልዩ የታካሚ እንክብካቤና አጠቃላይ ድጋፍ የሚያደርግ እንዲሁም የምክር እና የሥነ-ልቦና ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑ ተነግሯል።

በሆስፒታሉ ምክትል ዳይሬክተር እና የነርቭ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ያሬድ ዘነበ፤ ተላላፊ ያልሆኑና ረዥም ጊዜ የሚቆዩ በሽታዎች ሕክምና አሰጣጥ ላይ በሀገሪቱ ያለውን ክፍተት ለመሙላት፣ በግል ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ማዕከል መሆኑን ተናግረዋል።

ሆስፒታሉ በተለይም እንደ ካንሰር እና አልዛይመር በመሳሰሉ በሽታዎች ተጠቂ የሆኑ ታማሚዎችንና ቤተሰቦቻቸውን ከማገዝ አንፃር ታስቦ የራሱን ሚና እንዳለው ስለመቋቋሙ አንስተዋል።

ዘላቂ ለሆነ ጊዜ በሽታዎች የሚያጠቃቸውን ሰዎች አብዛኞቹ ቤተሰቦች ቤት ወስደው እንደሚንከባከቧቸው ያነሱት ዶ/ር ያሬድ፤ “ሆስፒታሉ ለሕመምተኞቹ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በሙሉ አሟልቶ በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎት ይሰጣል” ብለዋል።

ሌላኛው የሆስፒስ ማዕከል መስራች እና የውስጥ ደዌና የካንሰር ሰብ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ወንድማገኝ ጥግነት በበኩላቸው፤ ሆስፒታሉ ከአምስት ዓመታት በፊት በሀገራችን እውቅ በሆኑ ከፍተኛ ስፔሻሊስቶች መመስረቱን አንስተዋል።

የተለያዩ እህት ኩባንያዎችን በመክፈትም፤ አገልግሎቱን እያሰፋ ተደራሽ እየሆነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዚህም መሠረት ዘላቂ ሕመም ላለባቸው ሰዎች አገልግሎቱን ከውስጥ ደዌ ሕክምና ጋር በማቀናጀት መስጠት መጀመሩን አስታውቀዋል።

አገልግሎቱ በኢትዮጵያ በሚገኙ የግል ጤና ተቋማት ውስጥ ያልነበረና ለመጀመሪያ ጊዜ የተጀመረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ለሌሎች ተቋማትም አርአያ መሆን የሚያስችል ነው ተብሏል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...