ሕብረት ባንክ 35 ሚሊየን ብር  ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች አበረከተ

Date:

35 ሚሊዮን ብሩ የተሰጠው ለ10  የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ነው፡፡ድጋፍ የተርገላቸው አስሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የተመረጡት በሸሪዓው መርህ መሰረት የሚሰሩ መሆናቸው ተመዝኖ፣ ከሚደርሱት የሕብረተሰብ ቁጥር እና የሚሰጠውን ድጋፍ ለምን ተግባር እንደሚያውሉትም ጭምር ታይቶ ነው ተብሏል።

ድጋፉ ከተደረገላቸው ድርጅቶች መካከል፤ እማሙ ማሊክ ትምህርት ቤት፣ ወንድም ካሊድ ፋውንዴሽ፣ ባቡል ካኸር፣ ሜቄዶኒያ፣ ቢላሉ ሀበሺ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሙስሊም የጤና ባለሞያዎች ማህበር ይገኙበታል።

ሕብረት ባንክ የሸሪዓውን መርህ በተከተለ መልኩ ከወለድ ነፃ የባንክ እገልግሎት መስጠት ከጀመረ 10 ዓመታት እንዳለፈው አስታውሷል።

በአሁኑ ሰዓትም ሕብረት ባንክ 23 ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ብቻ የሚሰጡ ቅርንጫፎች ከፍቼ እየሰራሁ ነው ሲል  ጠቅሷል።

ባንኩ ሸሪዓው በሚያዘውና የሕብረት ባንክም እንዱ እሴት የሆነውን የመረዳዳት ወይም ማሀበራዊ ሃላፊነትን የመወጣት ተግባር ለመከወን  ሕብረት ከሚሰጠው የባንክ አገልግሎች በሻገር በማሕበረሰቡ ሕይወት ውስጥ በጎ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ  ማሕበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚሰሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ሲደግፍ መቆየቱን አስታውሷል።

ትናንት ምሽት በሸራተን ሆቴል በተካሄደው ድጋፍ መስጠት ዝግጅት ላይ የሴቶችና የማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፣ ሌሎች የመንግስት ሹመኞች እንዲሁም የባንኩ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...