መደበኛ ያልሆነን የጎዳና ንግድ ደንብ ወጣለት

Date:

የደንቡን መውጣት ተከትሎም ንግዱ የሚካሄድበት ሰዓት በአምስት ፈረቃ ተከፋፍሎ ይፋ ሆኗል።

በዚሁ መሰረት

📌 ከንጋቱ አስራ አንድ ሰዓት እስከ ንጋቱ አንድ ሰዓት የአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የአልባሳት እና መጫሚያዎች ንግድ እንደሚካሄድ ተነግሯል።

📌 ከንጋቱ አንድ ሰአት እስከ ረፋዱ ሶስት ሰዓት ደግሞ እንደ ብስኩት ፤ ሻይ ፤ ቡና ፤ የታሸገ ውሃ እና ለስላሳ መጠጦች ያሉ እና ለቁርስ የሚሆኑ ቀላል ያሉ ምግቦች ንግድ ይካሄዳል ተብሏል።

📌 የጫማ ፅዳት ወይም ሊስትሮ አገልግሎትም በዚሁ ሰዓት እንደሚሰጥ የከተማ አስተዳደሩ አመልክቷል።

📌 ከረፋዱ ሶስት ሰዓት እስከ ቀኑ ስድስት የመፅሃፍት ፤ መፅሄቶች እና ጋዜጦች ንግድ እንዲካሄድ ፤ ከቀኑ ስድስት ሰዓት እስከ ስምንት ሰዓት ደግሞ ፤ቀላል ምግቦች በመባል የሚታወቁት እንደ ኬክ ፤ ብስኩት ፤ ሻይ ፤ ቡና ፤ የታሸገ ውሃና ለስላሳ መጠጦች ንግድ እንዲካሄድ ታስቧል።

📌 ከምሽቱ አስራ አንድ ሰዓት እስከ ምሽቱ ሶስት ሰዓት ተኩል የተጠበሱ ምግቦች ፤ ጁስ ፤ ብስኩት ፤ ኬክ ፤ ሻይ ፤ ቡና ፤ የታሸገ ውሃ እና ለስላሳ መጠጦች ፤ እንዲሁም አልባሳት እና መጫሚያዎች ፤ ቀላል የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች ፤ የውበት መጠበቂያ ኮስሞቲኮስች እንዲሸጡ የከተማ አስተዳደሩ መርሃ ግብር አውጥቷል።

ንግዱ የሚካሄድባቸው ቦታዎች ወደፊት እንደሚለዩ የከተማ አስተዳደሩ ተናግሯል።

መደበኛ ያልሆነ የጉዳና ላይ ንግድ ኮንትሮባድን ያበረታታል፤ ለትራፊክ መጨናነቅ እና አደጋም መንስኤ ይሆናል እንዲሁም በህጋዊ ንግዱ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል በሚል ቁጥጥር እንዲደረግበት ሲሞከር የቆየ ነው፡፡

አሁን በከተማ አስተዳደሩ የቀረበው ሃሳብ ቀደም ሲል የነበሩ ችግሮችን ምን እንዴት ነው ያያቸው? ስንል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ለሆኑት አቶ ፍስሃ ጥበቡ ሸገር ሬዲዮ ጥያቄ አቅርበዋል።

አቶ ፍስሃ እንደሚሉት ኢ – መደበኛ በሆነው ንግድ የሚሸጡት ምርቶች በተለይ አልባሳትና ጫማዎች ከአገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች የተገኙ እንዲሆኑ ነው የታሰበው።

በኮንትሮባንድ የገቡ አልባሳት እና ጫማዎች ወደዚህ የንግድ ስርአት እንደማይገቡ ምን ዋስትና አለ?

አቶ ፍሰሃ በምላሻቸው የኢ – መደበኛ ንግድ ሌላው አሉታዊ ጎን በሚል የሚጠቀሰው በመደበኛ ንግድ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ነው።

ንግድ ፍቃድ አውጥተው፤ ግብር እየከፈሉ የሚሰሩ ነጋዴዎችን ተወዳዳሪነት ይጎዳል በሚል እንደሚነቀፍ ይታወቃል።

ይህንንስ እንዴት አይታችሁት ነው ስንል የቢሮውን ምክትል ህጋዊው ንግድ ፈጽሞ በዚህ አይጎዳም ሲሉ መልሰዋል።

የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች በሚል የተወሰነ አካባቢ ተለይቶ ኢ-መደበኛ ንግዱ እንዲካሄድ ከዚህ ቀደም ሙከራ እንደነበር ይታወሳል።

ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ ሰዎች ግን ቅዳሜ እና እሁድ ብቻ በተወሰነ አካባቢ በሚካሄደው በዚህ ንግድ ለመሳተፍ እምብዛም ፍላጎት እንደሌላቸው ሲነገር ቆይቷል።

ምክንያታቸው ደግሞ በዚህ ዓይነቱ ንግድ ብዙም ገበያ የለም ፤ አትራፊም አያደርገንም የሚል ነው፡፡

አሁንስ ወደ ተዘጋጁ ቦታዎች በመግባት በወጣው ፈረቃ ኢ-መደበኛውን ንግድ ለማካሄድ ሰዎች ምን ያህል ፍቃደኛ ሊሆኑ ይችላሉ ስንል የጠየቅናቸው አቶ ፍስሃ መግባት የሚፈልጉ ሰዎችን ብቻ እናስገባለን ብለውናል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...