መግለጫ የምንሰጠው ጦርነትን ለማስቆም እንጂ የሥልጣን ወንበር ለመንጠቅ አይደለም

Date:

‎በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ‎መግለጫ የምንሰጠው ጦርነትን ለማስቆም እንጂ የሥልጣን ወንበር ለመንጠቅ አይደለም ሲሉ የተለያዩ የፓለቲካ ፓርቲዎች ለአሐዱ አስታውቀዋል።

‎የእናት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሠይፈሥላሴ አያሌው፤ “መንግሥት እየሄደበት ያለው መንገድ ትክክለኛ ካልሆነ ለማሳወቅ የምንሞክረው በመግለጫ በመሆኑ እና በዜጎች ላይ የሚደረሱ ጥቃቶች እንዲቆሙ መንግስትን የምንጠይቅበት መንገድ ነው” በማለት ተናግረዋል።

“‎በዚህም የምንሰጣቸው መግለጫዎች በትክክል ውጤት ያመጣሉ የሚለውን በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም ነገር ግን ይደመጣሉ” ያሉት ዶክተር ሠይፈሥላሴ፤ “በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችን ለማስቆም በትብብር ከሚሰሩ ፓርቲዎች ጋርም ሆነ እንደ እናት ፓርቲ ያወጣነው መግለጫ ውጤት አላመጣም  ብሎ መናገር ይቻላል” ብለዋል።

“‎በሀገሪቱ ውስጥ የሚታየው ‘የኔ ብቻ’ የሚል የፓለቲካ አስተሳሰብ እንዲቀርና ዜጎች ከቦታ ቦታ በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ ለማድርግ እንዲሁም ሰላማዊ የሆነ የፓለቲካ ትግል እንዲኖር ፖለቲከኞች ጠንክረው የመስራት ሃላፊነት አለባቸው”  ሲሉም የፓርቲው ፕሬዝዳንት ገልጸዋል።

‎የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፓርቲ ፕረዚዳንት አቶ አብርሃም ጌጡ በበኩላቸው፤ “በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶችን እና ግጭቶችን ለማስቆም የምናወጣው መግለጫ በሀገሪቱ ፍትሕና ሰላም እንዲሰፍን ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

‎”መንግሥት ቢሰማንም ባይሰማንም እኛ ‘ጦርነት ይቁም!’ የሚል መግለጫ ባገኘነው አጋጣሚ ከመስጠት ወደኋላ አንልም፤ ነገር ግን ከምንሰጠው መግለጫ ትምርህት የሚወስድ አካል አለ” ሲሉ ተናግረዋል።

‎”በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረውንና ያለውን የፖለቲካ ሁኔታ ተገንዝበን በመተንተን ሰላማዊ የሆነ ትግል በመቀየስ፤ ሠላማዊ ከሆነው ትግል መካከል ድምፅን ማሰማት ነው” ያሉት የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ አብርሃም፤ በዚህም  በየጊዜው የምናወጣው መግለጫ አንዱ ሰላማዊ ትግል በመሆኑ የዜጎችን ችግር ለዓለም የምናሰማበት ነው በማለት ገልጸዋል።

‎የፓለቲካ ፓርቲዎቹ በሀገሪቱ ያሉ ጦርነትና ግጭቶች ሠላማዊ በሆነ መንገድ በውይይትና በምክክር ችግሮች እንዲፈቱ ብሎም ሀገሪቱ ያለችበትን ነባራዊና ተጨባጭ ሁኔታ ተከታታይ የሆነ መግለጫ ከመስጠት አንቆጠብም በማለት ገልጸዋል።

‎የትብብር ፓርቲዎች ሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በጋራ መግለጫ መሰጠታቸው የሚታወስ ነው።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አርሰናል ከቦርንማውዝ በጉጉት የሚጠበቅ ጨዋታ

በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ቀን...

በአሜሪካ እና ኢራን ድርድር ላይ የሚነሱ አራት ቁልፍ ጥያቄ

በፓኪስታን የሚደረገው የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር እየተጠበበፓኪስታን ነገር ግን...

መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችን ፈታኝ መሆኑን እናውቃለን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል...

የተመድ ዋና ጸሐፊ ኢራን እና አሜሪካ “በቅን ልቦና” ወደ ድርድሩ እንዲገቡ ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አሜሪካ እና ኢራን...