ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ በፅኑ እስራት ተቀጡ

Date:

የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፤ ባሳለፍነው ሳምንት በሁለት ክሶች ጥፋተኛ የተባሉት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ላይ 13 ዓመት ፅኑ እስራትና 21 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ፍርድ አስተላልፏል ።

ፍርድ ቤቱ የቀድሞዉ ከንቲባ ካቀረቡት 8 የቅጣት ማቅለያዎች 4ቱን በመቀበል እና አራቱን ዉድቅ በማድረግ ነዉ የ13 ዓመት ፅኑ እስራት የፈረደባቸው።

በዚሁ በእሳቸው መዝገብ ተከሳሽ የነበሩት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ታርኩ ታመነ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እነ 41 ሺህ ብር ፤ አቶ ታፈሰ ቱናሻ በ8 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራትና 51 ሺህ ብር እንዲሁም አቶ ሰይፉ ሌሊሴ የተባሉ ግለሰብ እንደዚሁ በ8 ዓመት ከ5 ወር እና 76 ሺግ ብር የገንዘብ ቅጣት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከባለፈው  ዓመት የ130 በመቶ ብልጫ  አተረፈ

መጋቢት 30 በተጠናቀቀው የኩባንያው በጀት ዓመት 15.9 ቢሊዮን ብር...

በዕውቀቱ በታላቁ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ተመረጠ

ዝነኛው ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...