ታዋቂው የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ ዶ/ር ዴቪድ ማትሳንጋ ግብጽ በኢትዮጵያ የውሃ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ የምታሳየውን ኃይለኛ ተቃውሞና ዛቻ አጥብቀው አወገዙ።
ግብጽ የናይልን ጉዳይ እንደ ፖለቲካ መሣሪያ እየተጠቀመችበት መሆኑን የገለጹት ተንታኙ፣ ሀገሪቱ ዛቻውን በመተው ስጋቶቿን ይዛ ወደ ድርድር ጠረጴዛ መምጣት እንዳለባት አሳስበዋል።
ኢትዮጵያ ፋብሪካዎችን ለማንቀሳቀስ እና የኢኮኖሚ እድገቷን ለማፋጠን ኤሌክትሪክ እንደሚያስፈልጋት የገለጹት ዶ/ር ማትሳንጋ፣ ወንዞቿ ወደ ውጭ ስለሚፈሱ ብቻ ልማቷን ልታቆም እንደማይገባ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ዓላማ ጎረቤት ሀገራትን መጎዳት ሳይሆን የውሃ ሀብቷን በፍትሃዊነት መጠቀም መሆኑንም ገልጸዋል።
በመጨረሻም ግብጽ ወታደራዊ ዛቻዎችን እና የጦርነት ንግግሮችን እንድታቆም አሳስበዋል። ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከመውሰድ ይልቅ፣ ሁለቱ ሀገራት ወደ አፍሪካ ህብረት በመመለስ በውይይት እንዲፈቱት ጥሪ አቅርበዋል።
FMC English
