“ሰከላ” የተሰኘ የትምህርት ተቋማት ዲጂታል መተግበሪያ ይፋ ኾነ

Date:

የትምህርት ተቋማት ወደ ዲጂታል አሰራር በሚያደርጉት ጉዞ የሚያስፈልጋቸውን ዘመኑን ያማከለ መተግበሪያዎች የያዘ ሰከላ “sekela Sims (school information management system)” የተሰኘ የትምህርት መተግበሪያ በዛሬው እለት በሰፕኢድ ኃ/የተ/የግ/ድርጅት እና BRDGE-ኢትዮጵያ ይፋ ሆኗል

ሰክላ የመማር ማስተማር ሂደትን ሙሉ ለሙሉ በኦንላይን ማድረግ ለሚሹ ተቋማት አይነተኛ መፍትሄ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በትምህርት ሚኒስቴር ካሪኩለም መሰረት እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ያሉትን መፅሐፍትና አጋዥ መፅሐፍትን በድምፅና በቪዲዮ በቪዲዮ የተዘጋጁ ማጣቀሻዎችን ተማሪዎች በስልክም ሆነ በታብሌትም ተጠቅመው ለመማር የሚያስችላቸውን የዲጂታል ላይብራሪዎችንም ያካተተ ነው

ሰከላ በሃገራችን የሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማትን ፍላጎቶች እና አወቃቀርን በማጥናት እንዲሁም ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሃገራት ካሉ የት/ት አስተዳደርና መረጃ አያያዝ ሶፍትዌሮች ተሞክሮ በመውሰድና ያሉትን ከፍተቶች በመሙላት ፣ የሀገር ውስጥ ሶፍትዌር አልሚዎች ከ ት/ት ፖሊሲ አውጭዎች ጋር በመተባበር የገነቡትና ከ89 በላይ በሆኑ የግልና የመንግስት የት/ት ተቋማት ላይ ተሞክሮ አስፈላጊው ማሰተካከያና ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ ወደ ስራ የገባ ፣ ከበርካታ የባንክ ስርአት ጋር የተጣመረና በሶፍትዌር ደህንነትና ጥራት በINSA ተፈትሾ ማረጋገጫ የተሰጠው መተግበርያ እንደሆነ ተገልጿል።

የሰከላ ሲስተም ከገጠር ት/ቤት እስከ ከተማ ያሉትን በኔትዎርክ በማገናኘት ሀገራዊ መረጃን በመሰብሰብ ተዐማኒነት ያለው መተግበሪያም ነው ተብሏል።

ሰከላ ሁሉንም ተደራሽ የሚያደርግ ሲሆን ሲስተሙን በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችም መጠቀም ያስችላል፡፡

ከሁሉም የባንክና የፋይናንስ ተቋማት ጋር በቀላሉ በማገናኘት ከፍያን ሙሉ ለሙሉ በየቅርንጫፍ ባንኮች ወይንም በቀጥታ በሲስተሙ ላይ ለመክፈል የሚያስችልም ነው፡፡

ሰከላ መተግበሪያ ማንኛውም የት/ት ተቋምም የዲፕሎይመንት አገዛ ሳይፈልግ በsekela.app ዌብሳይት ላይ በመመዝገብና መረጃን በማስገባት በጥቂት ቀናት ውስጥ ተቋሙን ለማዘመን የሚያስችል የ cloud system እንደሆነ ተነግሯል::

ሰከላ ባንኮች የክፍያ ስራታቸውን ከሰከላ ሲስተም ጋር ያለምንም ክፍያ በማያያዝ ወይም Integration በማድረግ ወደስራ መግባት የሚያስችላቸውም ነው።

ሰከላ ከባንኮች ጋር በሚያደርገው ጥምረት የአንድ ወገን ከፋይነት የሌላ ወገን ተከፋይነትን በማስወገድ በጋራ ወይም (win win) ጥምረትን የተከተለ በመሆኑ ከነበሩት የተለመደ partnership በእጅጉ የተለየና ሁለቱንም አካል እኩል ተጠቃሚም ትጠያቂም የሚያድረግ የገበያ ስርዓት ያለው ነው ተብሏል፡፡

ይኸ ጥምረት ሁሉንም ተቋማት የሚያጣምር ሲሆን፡ ቴሌኮም: በ connectivity እና በ infrastructure መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፡ ባለተደረሰባቸው ክልሎችና በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርት ለተቋረጠባቸው ቦታዎች የሚያደርጉትን ጥረት የሚያግዝ ሲስተም በመሆኑ በጋራ በመግባባት መስራት የሚያስችል ነው። #ድሬቲዩብ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...