ሲያከራክር የቆየው የገቢ ግብር አዋጅ ፀደቀ

Date:

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አፅድቋል።

ረቂቅ አዋጁ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።

አዋጁ ሰፊ ክርክር ሲነሳበት እንደነበር ይታወቃል።
በተለይም የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማሕበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የደመወዝ ገቢ ግብር መነሻ ተብሎ የተቀመጠው 2,000 ብር ወደ 8,324 ብር ከፍ እንዲል ፤ አጠቃላይ አዋጁ የኑሮ ውድነቱንና ጫናውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲታረም ሲወተውት ነበር።

የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ከመረመረ በኋላ፣ አዋጁን አፅድቆታል።

ረቂቅ አዋጁ በተለይም በንግዱ ማህበረሰብና በተቀጣሪ ሠራተኞች ላይ ሊጣል የታሰበው የግብር ምጣኔ ከፍተኛ ነው የሚል ቅሬታ ሲነሳበት እንደቆየ ተዘግቧል፡፡

ከተለያዩ ወገኖች የቀረቡት አስተያየቶች፣ አሁን ካለው የኑሮ ውድነትና የዋጋ ንረት አኳያ፣ እስከ 35 በመቶ የሚደርሰው የገቢ ግብር መጠን መቀነስ እንዳለበት ይጠቁማሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...