ስዊዘርላንድ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች በሥማይ ክልሏ ላይ እንዳይበሩ ከለከለች

Date:

የስዊዘርላንድ መንግሥት ከአይሁድ እና ከኢራን ጋር ተያይዞ አሜሪካ ያቀረበችለትን ወታደራዊ አውሮፕላኖች በሥማይ ክልሏ ላይ እንዲበሩ የተጠየቀውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል።

መንግሥት ባወጣው መግለጫ መሠረት ለአየር ክልል አጠቃቀም የቀረቡለትን አምስት ጥያቄዎች የመረመረ ሲሆን ከጦርነቱ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸውን ሁለት በረራዎች የሀገሪቱን የገለልተኝነት ሕግ የሚጥሱ በመሆናቸው ሳይቀበላቸው ቀርቷል።

ሆኖም ግን ከግጭቱ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ሶስት ሌሎች በረራዎች እንዲከናወኑ ፈቅዷል።

የስዊዘርላንድ የገለልተኝነት ሕግ በማንኛውም ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች ለጦርነት ዓላማ የሚጠቀሙባቸው በረራዎች በሀገሪቱ የአየር ክልል ላይ እንዳያልፉ ይከለክላል።

በተቃራኒው ለሰብአዊ ድጋፍ፣ ለህክምና አገልግሎት፣ የቆሰሉ ሰዎችን ለማጓጓዝ እንዲሁም ከጦርነቱ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ለሌላቸው በረራዎች ፈቃድ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

አሁን ላይ የተፈቀዱት ሶስት በረራዎች ሁለት የጭነት አውሮፕላኖችን እና አንድ የጥገና አውሮፕላንን የሚመለከቱ ሲሆን እነዚህም በውጊያ ስምሪት ላይ ያልተሰማሩ መሆናቸውን መንግሥት አረጋግጧል።

የስዊዘርላንድ ባለሥልጣናት ወደፊትም የሚቀርቡ መሰል ጥያቄዎች ከተለመደው የአየር ትራፊክ ፍሰት በላይ ከሆኑ ወይም የጉዟቸው ዓላማ በግልጽ ካልታወቀ ውድቅ እንደሚደረጉ አሳስበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...