ሶማሊያ ከ34 ዓመት በኋላ አየር መንገዷን ወደ ስራ ልትመልስ ነዉ

Date:

ሶማሊያ ከ34 አመታት በኋላ አየር መንገዷ ወደ ስራ ሊመለስ መሆኗን ስትገልፅ ሁለት የኤይርባስ A320 አውሮፕላኖችንም መግዛቷን አስታውቃለች።

የሃገሪቱ የትራንስፖርት እና ሲቪል አቪየሽን ሚኒስትር መሐመድ ፋራህ የአውሮፕላን ግዢው መፈፀሙን አረጋግጠው በቀጣይ ሁለት ወራት ወደ ስራ ይገባሉ ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም”ከ34 አመታት በፊት ስራ ያቆመውን የሶማሊ አየር መንገድን መልሰነዋል፤ ዛሬ በሁለት አውሮፕላን የጀመርነው ሶስት እያለ እየጨመረ ይሄዳል” ሲሉ ተደምጠዋል።

ሚኒስትሩ” በመላው አለም ያሉ የሶማሊ ማህበረሰብ የሌሎችን አየር መንገድ በመጠቀም ገንዘብ ያወጣሉ” ሲሉ የስራ ዕድል በመፍጠር እና በውጪ ሃገራት አየር መንገዶች ላይ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስ የሶማሊያን ኢኮኖሚ ያግዛል ብለዋል።

የሶማሊያ አየር መንገድ ምስረታውን በ1964 ያደረገ ሲሆን በ1991 በሃገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት ከተከሰተ በኋላ ስራውን አቁሟል።

የሶማሊያ አየር መንገድ ዳግም ወደ ስራ መመልስም በጦርነት የላሸቀውን ኢኮኖሚ እንዲያንሰራራ ከማገዙ በተጨማሪ የፈረሱ ብሔራዊ ተቋማት ወደ ስራ በመመለስ ረገድ የተጀመረውን ስራ የሚያጠናክር ነው ተብሏል።

Source: Eastleigh Voice
@tikvahethmagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አርሰናል ከቦርንማውዝ በጉጉት የሚጠበቅ ጨዋታ

በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ቀን...

በአሜሪካ እና ኢራን ድርድር ላይ የሚነሱ አራት ቁልፍ ጥያቄ

በፓኪስታን የሚደረገው የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር እየተጠበበፓኪስታን ነገር ግን...

መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችን ፈታኝ መሆኑን እናውቃለን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል...

የተመድ ዋና ጸሐፊ ኢራን እና አሜሪካ “በቅን ልቦና” ወደ ድርድሩ እንዲገቡ ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አሜሪካ እና ኢራን...