ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልበት ወደ አገር ስለገባ ዕቃ

Date:



(በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 130 መሰረት)
✅  ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆኖ ወደ አገር የገባን ዕቃ ቀረጥና ታክሱ ሳይከፈልበት ተመሳሳይ የቀረጥ የቀረጥ ነፃው መብት ከተሰጠበት ዓላማ ውጪ መገልገል ወይም በሌሎች ሰዎች ይዞታና አገልግሎት እንዲውል ማድረግ ቀረጥና  የተከለከለ ነው፤


✅  ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆኖ ወደ አገር የገባን ዕቃ ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልበት ተመልሶ ከአገር ሊወጣ ወይም ተመሳሳይ የቀረጥና ታክስ ነፃ መብት ላለው ሰው ሊተላለፍ ወይም ቀረጥና ታክሱ ተከፍሎበት ለሌላ ሰው ሊተላለፍ ይችላል፤ ቀረጥና ታክሱም የሚሰላው ዕቃው በተላለፈበት ጊዜ በሚያወጣው ዋጋና ፀንቶ ባለው የታሪፍ ልክ መሠረት ይሆናል፤


✅ ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልበት ወደ አገር ውስጥ የገባ ዕቃ የጠፋ ወይም ጉዳት የደረሰበት እንደሆነ አስመጪው ለኮሚሽኑ ይህንኑ ማሳወቅ አለበት፤
✅  ለኢንቨስትመንት ስራ የቀረጥና ታክስ ነፃ መብት የተሰጠው ሰው ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆነው የገቡ ዕቃዎችን ለሌላ ሰው ሲያስተላለፍ ወይም የኢንቨስትመንት ፈቃዱን ሲመልስ በቅድሚያ ከኮሚሽኑ የተሰጠውን የክሊራንስ ሰነድ የማቅረብ ግዴታ ይኖርበታል፤


✅  የሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ ወይም መዝጋቢ አካልም በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (4) የተደነገገው ሁኔታ መሟላቱን የማረጋገጥ እና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሁኔታዎች መኖራቸውን እንዳወቀ ለኮሚሽኑ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፤


✅  ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልበት ወደ አገር የገባን ዕቃ በዋስትና ማስያዥ የሚቻለው ከኮሚሽኑ ጋር በቀረጥና ታክሱ አከፋፈል ረገድ ስምምነት ላይ ሲደርስ ይሆናል፤


✅ የባለቤትነት ስም ዝውውር የሚመዘገብ ማናቸውም አካል ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለበትን ዕቃ ሲመዘገብ ይህን በባለቤትነት የምስክር ወረቀት ላይ መግለፅ ያለበት ሲሆን ዕቃው ለሶስተኛ ወገን በሚተላለፍበት ጊዜ ቀረጥና ታክሱ መከፈሉን የማረጋገጥ ግዴታ አለበት፤ 
***********                                                                                                                                                                       

የደንበኞች ትምህርት ቡድን
መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም
ምንጭ፡- ጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት ገለጸች

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት የአገሪቱ...

ከትግራይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎች ካልወጡ ተማሪ አንመድብም

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና...

ኢራን አሜሪካ የጣለችባት ዕገዳ የበለጠ የሚጎዳው ዋሽንግተንን ነው አለች

አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የኢኮኖሚ እና የባሕር እንቅስቃሴ እገዳ...

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...