
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በአምባሳደሩ ኤርቪን ማሲንጋ አማካኝነት መልዕክት አስተላልፏል።
በህገወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ መግባት፣ ቪዛ ለማግኘት መዋሸት፣ ያለ ህጋዊ የስራ ፍቃድ ስራ መስራትና የቪዛ ጊዜ ካበቃ በኋላ በአሜሪካ መቆየት ከባድ ቅጣት ያስከትላል።
ቅጣቶቹ እስርን፣ ወደ ሃገር መመለስን እና ዳግም ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ መከልከልን እንደሚያካትት ነው አምባሳደሩ የተናገሩት።
አክለውም፥ “በህገ ወጥ መልኩ በአሜሪካ የሚኖር ቤተሰብ ወይም ጓደኛ ካላችሁ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የምትነግሩበት ጊዜ አሁን ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
መልዕክቱ፥ የአሜሪካ መንግስት ሌሎች በህገወጥ መንገድ እንዲገቡ የሚተባበሩት ላይም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።
አሜሪካ በቅርቡም ህገወጥ ስደትን መከላከል አልቻሉም ባለቻቸው የሃገራት ባለስልጣናት ላይ የቪዛ ገደብ መጣሏን አስታውሰዋል።
በህገወጥ መንገድ መግባት ከሚያስገኘው ጥቅም በላይ ጉዳቱ ያመዝናል ያለው ኤምባሲው ዜጎች የወደፊት ህይወታችን ከመጉዳት እንዲታጠቀቡ እና በህገወጥ መንገድ በአሜሪካ ያሉ ቤተሰቦቻቸውንም በጊዜ እንዲመለሱ ጥሪ እንዲያደርጉ አምባሳደሩ አሳስበዋል።
@Tikvahethmagazine