በሕዝብ ትራንስፖርት ውስጥ በሴቶች ላይ የሚፈጸመውን ፆታዊ ትንኮሳ ለመከላከል የሚያስችልአዲስ አዋጅ ሊጸድቅ ነው

Date:


በሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ውስጥ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ፆታዊ ትንኮሳ ለመከላከል የሚያስችል አዲስ አዋጅ ሊጸድቅ መሆኑን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሴቶች መብት ጥበቃና ምላሽ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ተወካይ ዘካሪያስ ደሳለኝ ለአሐዱ እንደገለፁት፤ ባለፈው በጀት ዓመት በተካሄደ የዳሰሳ ጥናት በዘርፉ ክፍተቶች በመስተዋላቸው አዲስ የሕግ ማዕቀፍ እንደሚያስፈልግ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

የሴቶችን ፆታዊ ጥቃት ለመከላከል በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ያስታወሱት ሥራ አስፈጻሚው፤ በተለይ በሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ላይ ጾታዊ ጥቃት የሚፈጽሙ አጥፊዎችን የሚቀጣ ሕግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

“ጥቃቱ የሚፈጸመው በሴቶች ላይ ብቻ ሳይሆ በወንዶችም ላይ ነው” ያሉት መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ “ድርጊቱ ከሥነ-ምግባርም ሆነ ከእሴት ያፈነገጠ በመሆኑ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ ቅጣት እንዲጣል በደል የደረሰባቸው ሰዎች በፌዴራል ደረጃ ለተቋቋመው ግብረ ኃይል መክሰስና መጠቆም ይጠበቅባቸዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

ማንኛውም ሰው በሕዝብ ትራንስፖርት አካባቢ ደህንቱ የተጠበቀ እንዲሆን እየተሰራ ቢሆንም፤ እንደዚህ አይነት ትንኮሳ የሚደረስባቸው ሴቶች ጉዳዮን ለሚመለከተው አካል አለመናገራቸው ቁጥጥሩን ወይም የመከላከል ሥራውን ከባድ እንዳደረገውም መሪ ሥራ አስፈፃሚው አስታውቀዋል።

በየጊዜው የሚወጡት ሕጎች፤ አዋጆች እና ፖሊሲዎች በትምህርት ቤት፣ በትራንስፖርት እና በየመስሪያ ቤቱ የሴቶችን ፆታዊ ትንኮሳ ለመከለል እና ለማስቀረት የሚያግዙ ሕጎች ስለመኖራቸው የገለጹም ሲሆን፤ ሕገ-መንግሥቱም ቢሆን ድርጊቱን በፅኑ እንደሚያወግዘው አክለዋል።

ጥቃቱን ለመከለከል የሚወጡ ሕጎችን ተግባራዊ ማድረግ እና የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ሚና መሆኑንም ጨምረው ለአሐዱ ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከባለፈው  ዓመት የ130 በመቶ ብልጫ  አተረፈ

መጋቢት 30 በተጠናቀቀው የኩባንያው በጀት ዓመት 15.9 ቢሊዮን ብር...

በዕውቀቱ በታላቁ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ተመረጠ

ዝነኛው ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...