ሶስት አፍሪካውያን የዓለም እግር ኳስ ከዋክብት እግር ኳስን ለእርቅና ለዘላቂ ሰላም መጠቀም ባህል እዲሆን ለማበረታታት በኢትዮጰያ አየር መንገድ ወደ ሶማሊያ ተጉዘው በሞቃዲሾ ስታዲየም ጨዋታ አድርገዋል።
ናይጄሪያዊው ጄጄ ኦካቻ፤ ካሜሩናዊው ሳሙኤል ኤቶ እና ቶጎአዊው ኢማኑዌል አዴባዮር “እግር ኳስን በመጠቀም ሰላምን ማስፈን” በሚል በፊፋ የተጀመረውን የሰላም ጉዞ በመቀላቀል ሶማሊያ ገብተው ዛሬ በሞቃዲሾ ስታዲየም ጨዋታ አድርገዋል።
እንደ ሲጂቲኤን ዘገባ፥ ከዋክብቱ ወደ ሶማሊያ ያቀኑት ሀገሪቱ በስፖርት ዘርፍ እያስመዘገበችው ያለውን ዕድገት ተከትሎ እግር ኳስን ለእርቅና ለዘላቂ ሰላም እንደመሳሪያ እንድትጠቀም ለማበረታትና መልካም ገፅታዋን ለመመለስ ነው።
