በሞባይል ባንኪንግ ወንጀል በተጠረጠሩ 80 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረ

Date:

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት ከ116 ግለሰቦች ላይ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በሞባይል ባንኪግ በማጭበርበር ወንጀል በተጠረጠሩ 80 ግለሰቦች ላይ፣ ወንጀል ምርመራ በማጣራት፣ክስ እንዲመሰረት ማድረጉ ተገለጸ፡፡


‎ተከሳሾቹ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ከሌሎች የግል ባንኮች የሚደውሉ በማስመሰል እንዲሁም የኮምፒውተር ስርዓትን በመጠቀም አሳሳች መረጃዎችን በማሰራጨት ወንጀሉን እንደፈጸሙ ፖሊስ አስታውቋል።


‎የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረበው ክስ እንደሚያብራራው፣ ተጠርጣሪዎቹ ማንነታቸውን በመሰወር፣ ሀሰተኛ ሰነዶችንና መታወቂያዎችን በማዘጋጀትና በመጠቀም የተበዳዮችን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው በምርመራ ተረጋግጧል።

‌‎
‎ለወንጀል ድርጊቱ ማስፈጸሚያነት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ በርካታ የባንክ አካውንቶች፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ ሲም ካርዶችና ኮምፒውተሮች የተያዙ ሲሆን፣ ጉዳዩን ለማጣራት ተጨማሪ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር ተቋም ላይ ጥቃት ለማድረስ ዛቱ

አሜሪካ በኢራን ላይ የምታደርሰው ጥቃት 11ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዝዳንት...

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአሜሪካ ” American Space ” ማዕከል ተመረቀ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቨን ማሲንጋ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመውን "American...

አሐዱ ባንክ ለ 8ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ

አሐዱ ባንክ ሥራ የጀመረበትን 4ኛ ዓመት በማስመልከት የተለያዩ ኩነቶችን...

ዕንባ ጠባቂ ከቀረቡለት አቤቱታዎች 84% በመንግስታዊ ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸው

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በተጠናቀቀው የ2018 በጅት ዓመት...