በሦስት ክልሎች የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ሊቋቋም ነው

Date:

በቀጣዩ የበጀት ዓመት በሦስት ክልሎች የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን እንደሚያቋቁም የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን አስታወቀ።

ሦስቱ ክልሎች አማራ፣ ኦሮሚያና ሲዳማ መሆናቸውን የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ አያሌው ተናግረዋል።

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በገቢዎች እና ጉምሩክ ቅሬታ ያላቸዉ ሰዎች መጀመሪያ ቅሬታቸዉን በተቋሙ አቅርበዉ ተቋሙ ምላሽ ካልሰጣቸዉ በይግባኝ ቅሬታቸዉን ተቀብሎ ዉሳኔ እንዲያገኙ እንደሚያደርግ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።

ኮሚሽኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከሶስት ነጥብ አምስት ቢሊየን ብር በላይ የዳኝነት ዉሳኔዎችን ማስተላለፉንም ገልጸዋል።

በዚህም በወራቱ ከተከፈቱ አንድ ሺህ 144 መዝገቦች መካከል 686 መዝገቦች ውሳኔ አግኝተዋል ሲል ፕረስ ድርጅት ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...