በበርበራ እና በአዲስ አበባ መካከል ቀጥታ በረራ በቅርቡ እንደሚጀመር ተጠቆመ

Date:

የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ የበርበራ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጎብኝተዋል። በዚህ ወቅትም አየር ማረፊያው አሁን ላይ ለዓለም አቀፍ ንግድ ክፍት መሆኑን መሆኑ ተገልጿል።

የሶማሊላንድ የአቬሽን ሚኒስትሩ ፉአድ አህመድ ኑኡስ በበርበራ እና በአዲስ አበባ መካከል የካርጎ እና የመንገደኞች በረራ በቅርቡ እንደሚጀመር አረጋግጠዋል።

በዚህም በርበራን ከአዲስ አበባ ጋር በማስተሳሰር ሶማሊላንድ፥ የዓሳ እና ሌሎች ምርቶች በበርበራ ኤርፖርት ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ያስችላታል ተብሏል።

በአዲስ አበባ እና በርበራ መካከል የሚደረገውን ጉዞ ቀላል በማድረግ የንግድ እና ቱሪዝምን እድገቱን ለማስፋትም ታቅዷል።

ዘገባው የሶማሊላንድ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...