በ50 ሚሊዮን ብር ሎተሪ የመጀመሪያ ዕጣ ከ 50 ሚሊዮን ብር ጀምሮ የ25 ሚሊዮን ብር ፤ የ10 ሚሊዮን ብር ፤ 5 ሚሊዮን ብር እና የተለያዩ የሚሊዮን ዕጣዎች መውጣታቸው ይታወሳል፡፡
በዚህም በአንድ ጀምበር ከ12 በላይ ሚሊዮነር ያደረገው የ50 ሚሊዮን ብር የሎተሪ ዕጣ አሸናፊዎች ታውቀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ መልክ የቤት እና የመኪና ዕጣዎች ከተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት ጋር ያቀረበው ቶምቦላ ሎተሪ ባለፈው ሰኔ 29 አሸናፊዎቹ ይፋ ማድርጉ ይታወቃል፡፡
በቶምቦላ ሎተሪ 1ኛ እና 2ኛ ዕጣ ባለ3 እና ባለ2 መኝታ መኖሪያ ቤት ዳጎስ ካለ ከተጨማሪ የገንዘብ ጉርሻ ጋር ለሽልማት አቅርቦ ዕድለኞችን በጉጉት ሲጠባበቅ ነበር፡፡
የ50 ሚሊዮን ሎተሪ እና የቶምቦላ ሎተሪ አሸናፊወች ሽልማታቸውን ቅዳሜ ሐምሌ 19/2017 ዓ.ም ከጥዋት 3፡00 ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል ‹‹የአሸናፊዎች ቀን›› በሚል ስያሜ በተሰጠው መርሀ-ግብር በይፋ ሽልማታቸውን ተረክበዋል፡፡
የሚሊዮን ሎተሪ ዕድለኞች
ተ.ቁ ስም አድራሻ የብር መጠን
1 የሽቱ ምስጋናው ከጎንደር 50 ሚሊዮን
2 ካሳ አለሙ አባይ ከአ.አ 25 ሚሊዮን
3 ዝናሽ ጌታቸው ደምሴ ደብረ ብርሃን 3 ሚሊዮን
4 ዮናስ ሰይፈ ከደብረ ብርሃን 3 ሚሊዮን
6 አቶ ታከለ ወርቁ ከሃዋሳ 1.5 ሚሊዮን
7 እሸቱ አበራ ከአ.አ 5 ሚሊዮን
8 ዘነበ አበበ ከአ.አ 5 ሚሊዮን
8 እድሪስ አብዱ ከአ.አ 2.5 ሚሊዮን
9 ሰውአለም መግራ ገመዳ ከደብረ ብርሃን/ጫጫ/ 7 ሚሊ
የቶምቦላ ዕድለኞች
1 ነጋልኝ አበራ ብሩ ከኦሮሚያ ም/ሸዋ 1ኛ ዕጣ ባለ 3 መኝታ መኖሪያ ቤት ከተጨማሪ ለ3ዓመት 60ሺህ
2 ቶምቦላ ወስላሴ 2ዕጣ ባለ 2 መኝታ መኖሪያ ቤት ከተጨማሪ ለ2ዓመት የሚቆይ 40ሺህ ጋር
3 ተስፋሁን ሀይሉ ከአ.አ 3ኛዕጣ አሸናፊ ቮልስዋገን መኪና ከተጨማሪ ለ 2 ዓመት የሚቆይ 20 ሺህ ብር አሸናፊ።
4 ኮሚሸነር ወርቅነህ በቀለ BYD suv አሸናፊ ከተጨማሪ ለ 2 ዓመት የሚቆይ 15 ሺህ ብር ጋር።
