በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉ አንዳንድ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ጽ/ቤቶች ታጥፈዋል

Date:

የከተማዋ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በ2017 በጀት አመት በከተማ አስተዳደሩ የማእከል ፣ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አደረጃጀቶች ውጤታማነት ላይ ጥናት ሲያካሄድ መቆየቱንና በጥናቱ መሰረት አንዳንድ አደረጃጀቶች እንዲታጠፉ መወሰኑን ውሳኔውን ለማስፈጸም ቢሮው ከጻፈው ደብዳቤ ላይ ለመመልከት ችሏል።

በጥናቱ መሰረትም አንዳንድ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አደረጃጀቶች ላይ ማሻሻያ መደረጉን አሳውቋል።

° በዚህም መሰረት በክፍለ ከተማ ደረጃ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ታጥፎ በቡድን ደረጃ በዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ስር እንዲደራጅ።

° የስራ አስኪያጅ ፑል እና የዋና ስራ አስፈጻሚ ሦስት አማካሪ መደቦች አደረጃጀታቸው እንዲታጠፍ።

° በወረዳ ደረጃም ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፣ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቅ/ጽቤት ፣ባህልና ኪነጥበብ ጽ/ቤት፣ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት እና ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት እንዲታጠፉና ስራው በክፍለ ከተማ ደረጃ እንዲከናወን።

° የወረዳው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት እና የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት በማዋሃድ በከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት የሚከናወኑ ተግባራት በጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት እንዲከናወኑ እና የ ጽ/ቤቱ ስያሜ ” የጽዳትና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት ” በሚል እንዲደራጅ።

° የዋና ስራ አስፈጻሚው አማካሪ አደረጃጀት እንዲታጠፍ ተወስኗል።

ውሳኔው ከሃምሌ ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ የሚያዝ ሲሆን እንዲታጠፉ ውሳኔ የተላለፈባቸው ጽ/ቤቶች እና አደረጃጀቶች መዘጋት መጀመራቸውን  ከሰራተኞቹ ለማረጋገጥ ችሏል።

እንዲታጠፉ ውሳኔ የተላለፈባቸው ጽ/ቤቶች ተዘግተው  ተገልጋዮችም ወደ ክፍለ ከተማ በመሄድ አገልግሎቱን እንዲያገኙ እየተነገራቸው ስለመሆኑ ስሜ አይጠቀስ ካሉ የግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ጽ/ቤት ባለሞያ ተናግረዋል።

ባለሞያዋ በሌላ ክፍል ድልድል እስኪከናወንላቸው ድረስ ስራ ሳይገቡ በቤት እንዲቀመጡ የተነገራቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ” ከስራ አለመባረራችንን እና የሃምሌ ወር ደሞዝም እንደሚገባልን ተነግሮናል ” ያሉ ሲሆን ድልድሉ እስኪከናወን በትዕግስት እንዲጠብቁ እንደተነገራቸው አመልክተዋል።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር ተቋም ላይ ጥቃት ለማድረስ ዛቱ

አሜሪካ በኢራን ላይ የምታደርሰው ጥቃት 11ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዝዳንት...

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአሜሪካ ” American Space ” ማዕከል ተመረቀ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቨን ማሲንጋ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመውን "American...

አሐዱ ባንክ ለ 8ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ

አሐዱ ባንክ ሥራ የጀመረበትን 4ኛ ዓመት በማስመልከት የተለያዩ ኩነቶችን...

ዕንባ ጠባቂ ከቀረቡለት አቤቱታዎች 84% በመንግስታዊ ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸው

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በተጠናቀቀው የ2018 በጅት ዓመት...