በኢራን የሚገኝ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እስራኤል ጥቃት ከጀመረችበት አርብ ጀምሮ የደረሱ ጉዳቶችን ሲከታተል መቆየቱን ገልጿል።
እንደ ሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ዘገባ ከሆነ 224 ንፁሀን ዜጎች ሲገደሉ 188 ቆስለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ 109 የኢራን ጦር ሠራዊት አባላት ሲገደሉ 123 ደግሞ ቆስለዋል ብሏል።
እስካሁን ማንነታቸው ያልታወቁ 119 ሰዎች መገደላቸውን እና 335 መቁሰላቸውን የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ አስታውቋል።
ይህም የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ የመዘገባቸው ሞቶችን ቁጥር 452 ሲያደርሰው 646 ቆስለዋል ብሏል።
የኢራን መንግሥት መገናኛ ብዙኃን እስካሁን በእስራኤል ጥቃት ስለተገደሉት ሰዎች መንግሥት ከገለፀው ውጪ ምንም ያሉት ነገር የለም።
BBC Amharic
