በኤአይ የተሰራው “ዎክ ማይ ዎክ” ሀገርኛ ዜማ በሳምንቱ የሙዚቃ ሽያጭ ሰንጠረዥ ከፍተኛውን ደረጃ ያዘ

Date:

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራው “ዎክ ማይ ዎክ” የሚለው ሀገርኛ ዜማ በአሜሪካ በሳምንቱ የሙዚቃ ሽያጭ ሰንጠረዥ ከፍተኛውን ደረጃ መያዙ ተገለፀ።

በወንድ ልጅ የድምፅ ዜማ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ተቀነባብሮ የተሰራው ሙዚቃው ተወዳጅነትን ማትረፉ በአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

ሙዚቃው በሳምንቱ በዲጂታል ሽያጭ በአሜሪካ የሀገርኛ ዜማዎች ዝነኛ እና ታዋቂ ከሆኑት ሥራዎች ተርታ መሰለፍ ችሏል፡፡

ዜማው ከሌሎች አርቲስቶች ድምፅና ምስል ጋር ምንም ዝምድና የሌለው ሲሆን፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ብቻ የተቀነባበረ የፈጠራ ሥራ መሆኑ የተለየ ያደርገዋል ሲል ቲአርቲ ዎርልድ መዘገቡን ኢቢሲ መዝናኛ  አስነብቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...