በውላችን መሰረት 60% ቀሪ ክፍያና የ4 ቀናት የቅድመ ስምሪት ወጪ እስከዛሬ አተፈጸመም

Date:

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በተለያዩ ክልሎች በምርጫ አስፈጻሚነት የተሰማሩ ዜጎች የሰሩበት ከግማሽ በመቶ በላይ ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው፣ በተፈጸመው ክፍያም ቢሆን የሰሩበት ቀን የተቀነሰባቸው እንዳሉና ምርጫ ቦርድ መፍትሄ እንዳልሰጣቸው ገለጹ።

“‎ በውላችን መሰረት ያልተከፈለው 60% ቀሪ ክፍያና የአራት ቀናት የቅድመ ስምሪት ወጪ እስከዛሬ ድረስ አተፈጸመም ” ብለዋል።

” በተደጋጋሚ የተሰጡ ቀጠሮዎች ሳይፈጸሙ ቀርተዋል ” በማለትም ወቅሰዋል።

በምርጫው ” በታማኝነት፣ በትጋትና በሙሉ ኃላፊነት የሰራን የምርጫ አስፈጻሚዎች ነን። ሀገራዊ ግዴታችንን በአግባቡ ተወጥተናል፤ ግን የሚገባንን ክፍያ እስካሁን አላገኘንም ” ሲሉ ገልጸዋል።

” ‘ከሐምሌ 11 እስከ 15/2018 ክፍያው ይፈጸማል'” ተብሎ እንደተገለጸላቸው አስታውሰው፣ ሆኖም ” ሐምሌ 18/2018 ቢያልፍም ምንም ክፍያ አልተፈጸመም። ይህ ሁኔታ በምርጫ ቦርዱ ላይ ያለንን እምነት እየሸረሸረ ይገኛል ” ብለዋል።

በአማራ ክልል በተለይ ሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ ምርጫ አስፈጻሚዎች ደግሞ፣ እስከ ሰኔ 2018 ዓ/ም ሙሉ ክፍያ ይፈጸማል ቢባሉም አለመፈጸሙን፣ 40% ክፍያ ሲፈጸምላቸውም ቢሆን የሰሩባቸው ቀናት መቀነሳቸውን ተናግረዋል።

አንድ የምርጫ አስፈጻሚዎች አስተባባሪ በሰጡን ቃል፣ ” እኛ ጋ የመጣው የጣቢያ አስፈጻሚዎች ክፍያ የ54 ቀናት መሆን እያለበት የ39 ቀናት ነው። በየወረዳው ላሉ ሦስት፣ ሦስት የምርጫ ክልል አስፈጻሚዎች ክፍያ ደግሞ መሆን የነበረበት የ169 ቀናት ነው፤ ግን የ79 ቀናት አልታሰበም ” በማለት ተናግረዋል።

40 በመቶ ክፍያ ሲፈጸምላቸው የ39 እና የ90 ቀናት ብቻ መሆኑን፣ 60 በመቶ የሚሆነው ክፍያ ደግሞ ጭራሽ እንዳልተፈጸመ ገልጸው፣ ” የኛ ብቻ ቀኑ የሚቀነስበት ምክንያት ምንድን ነው? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ቅሬታ አቅራቢዎች፣ ‎ክፍያቸው መዘግየቱና ሙሉ በሙሉ አለመከፈሉ ቤተሰቦቻቸው ጭምር ኢኮኖሚያዊ ጫና መፍጠሩን በመጥቀስ፣ ‎የሚመለከታቸው አካላት ውዝፍ ክፍያውን በአስቸኳይ እንዲፈጽሙና ለአስፈጻሚዎች ግልጽና ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ በጽኑ አሳስበዋል።

ቅሬታቸውን ይዞ ከምርጫ ቦርድ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ ስልክ ባለመነሳቱ ያልተሳካ ሲሆን፣ ሙከራው ይቀጥላል።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አዲስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ኢራን የበለጠ ምላሽ በመስጠት የተራዘመ ጦርነት እንደምታካሂድ አስታወቀች

ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አሜሪካ ሌላ ዙር ጥቃት በአገራቸው...

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሥራ ቡድን ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን...

የጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ 28 የውጭ ዜጋ ተማሪዎችን ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር ማስተሳሰሩን ገለጸ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ መርሃ-ግብር አማካኝነት በዘንድሮው ዓመት...

የሕግ ተማሪዎቹ አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት...