በዓለም አቀፍ ደረጃ በአይን ጤና ችግር  55 በመቶ ሴቶች ናቸዉ

Date:

12ኛው የምስራቅ፣ ማዕከላዊና ደቡባዊ አፍሪካ የዓይን ሕክምና ኮሌጆች ማህበራት ሕብረት (COECSA) የሳይንስ ጉባኤ እና የኢትዮጵያ የዓይን ሕክምና ባለሙያዎች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል መካሄድ ጀምሯል።

በዚህ ጉባዔ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከምስራቅ አፍሪካ፣ ከመካከለኛው አፍሪካ፣ ከደብብ አፍሪካ፣ ከአውሮፓ፣ ከእስያ እና ከሰሜን አሜሪካ የተውጣጡ የ12 ሀገራት የሕክምና ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ በአህጉሪቱ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለውን የአይን ጤና ችግር ለመቅረፍ ያለመ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

በጉባኤው ላይ ከ30 በላይ የምርምር ጥናቶች፣ ከ80 በላይ በሆኑ የተለያዩ ርዕስ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ሙያዊ ምክክሮች፣ የአይን ጤና አገልግሎት ሥራ አመራርን አገልግሎትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ሙያዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ውይይቶች እየተካሄዱ ነው።

በዚህም መድረክ ላይ “በኢትዮጵያ 80 በመቶ የሚሆነውን የአይን ጤና ችግር ማዳን ይቻላል” የሚል ጥናት የቀረበ ሲሆን፤ ነገር ግን አሁን የሀገሪቱን የአይን ጤና ለማሻሻል በርካታ ሥራዎች መስራት ይጠበቃል ተብሏል።

“በዓለም አቀፍ ደረጃ የአይን እይታ ችግር በፋይናንስ ሥርዓቱ ላይ ዋና ተግዳሮት እየሆነ ይገኛል” የተባለም ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ 411 ቢሊዮን ዶላር እንደሚታጣ ተነግሯል።

ስለዚህ በሽታውን ለመከላከል ሆነ ታማሚዎችን ወደ አይን ስውርነት ከማምራታቸው በፊት በሕክምና እርዳታ ለመታደግ የጤና አገልግሎቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ማጠናከር ይጠይቃል ተብሏል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓይን በሽታዎች ከሚሰቃዩት ሰዎች መካከል 90 በመቶዎቹ የሚኖሩት በደሀ እና በመካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ ስለመሆኑም በጉባዔው የተጠቆመ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል 73 በመቶ ያህሉ ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ ናቸው ተብሏል፡፡

በተጨማሪ በአይን ጤና ችግር ተጋልጠው ከሚገኙ ሰዎች መካከል 55 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው በጉባኤዉ ተመላክቷል።

ለዚህ ችግር በተለየ በአፍሪካ ሀገራት ዋናኛ ምክንያት የሆነው ደግሞ ድህነት፣ የእርስ በርስ ግጭትና ጦርነት፣ የአየር ንብረት መዛባት እንደሆነ ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ በተካሄደ የዓይን ጤና ሁኔታ ቅኝት ትንተና ላይ ተንተርሶ በወጣው የ2013/2014 ትንበያ ግምት ሰነድ መሠረት፤ ኢትዮጵያ በዓይን ጤና ችግር ጫና ከሰሀራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ሁሉ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡

በዚህም የሕብረተሰብ ጤና ቅኝት ትንበያ መሠረት ከ6 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የዓይን በሽታዎች መዘዝ ለዕይታ ችግር መጋለጣቸው ተመላክቷል፡፡

በዚህ ጉባዔ ላይ ከ650 በላይ ከ650 በላይ የአይን ሕክምና ባለሙያዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የጤና ማህበራት ተወካዮች እየተሳተፉ ሲሆን፤ ዛሬን ጨምሮ እስከ አርብ ነሐሴ 16 2017 ድረስ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...