በጋሞ ዞን በደረሰ የናዳና የጎርፍ አደጋ የ30 ሰዎች ህይወት አለፈ

Date:

በጋሞ ዞን አስተዳደር ስር በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች፣ በተለይም በደጋማ ስፍራዎች በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ በተከሰተ ድንገተኛ የናዳና የጎርፍ አደጋ የ30 ወገኖች ህይወት ማለፉ ተነገረ።

የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ይፋ እንዳደረገው፣ ይህ የተፈጥሮ አደጋ በሰው ህይወት ላይ ካደረሰው መሪር ጉዳት በተጨማሪ በንብረትና በአካባቢው ማህበረሰብ መደበኛ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል።

የአስተዳደሩ አካላት በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ፣ ለሟች ቤተሰቦችና ለዞኑ ህዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል።

በአሁኑ ወቅት በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም እንዲሁም መሰል ተጨማሪ አደጋዎች እንዳይከሰቱ አስፈላጊው የክትትልና የድጋፍ ስራ በከፍተኛ ትኩረት እየተከናወነ ይገኛል።

በመሆኑም ህዝባችን ወቅቱን ያገናዘበ ጥንቃቄ በማድረግና ከአደጋ ስጋት ቀጠናዎች በመራቅ ራሱንና ቤተሰቡን ከተፈጥሮ አደጋዎች እንዲጠብቅ ጥብቅ መልዕክት ተላልፏል። ለወገኖቻችንም ነፍስ ይማር እንላለን።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...