ባለስልጣኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለማቀፍ ዕውቅና አግኝቻለሁ አለ

Date:

የኢትዮጵያ ምግብና መድሐኒት ባለስልጣን የዓለማቀፉ የአክሪዲቴሽን ቦርድ ማረጋገጫ የሆነውን የ ISO 17025/2017 ዕውቅናን ከኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት መቀበሉን ይፋ አድርጓል።

ባለስልጣኑ በምግብ ደህንነትና ጥራት ቁጥጥር እና ህግ ማስፈፀም ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለማቀፍ ዕውቅና ማግኘቱን ከማሳወቁ በተጨማሪ በመድሐኒት ጥራት ላቦራቶሪ የተገኙ ዕውቅናዎችን ማስቀጠል እንደቻለ ነው የገለፀው።

የኢትዮጵያ ምግብና መድሐኒት ባለስልጣን ዓለማቀፍ ዕውቅና እንደተሰጠው ይፋ ባደረገበት መርሐ ግብር ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባን ጨምሮ የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ ባለስልጣን ተቋሙ የተሰጠው ዕውቅና በዘርፉ ለጥራትና ቁጥጥር የተሰጠውን ትኩረት እንደሚያሳይ ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ በበኩላቸው፣ አዳዲሶቹንም ሆነ ነባር ዕውቅናዎችን የማስቀጠሉ ሥራ በተቋሙ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ በመሰራቱ የተገኘ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም በመድሐኒት ጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ የመጀመሪያው ዓለማቀፍ ዕውቅና መገኘቱን ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሯ፣ በኮንዶም ጥራት ምርመራ በ2012 ዓ.ም በ5 መለኪያዎች፣ በምግብ ጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ እንዲሁም፤ በሕክምና ጓንት ጥራት ምርመራ የተገኙትን ዕውቅናዎች ማስቀጠል ስለመቻሉ ተናግረዋል።

የኢትየጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን እነዚህን ዕውቅናዎች ማግኘቱ ለተቋሙ ዓለማቀፍ ተወዳዳሪነትና ተቀባይነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...