ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ጨምሮ ከቅዱስ ሲኖዶስ የቀረበውን ጥያቄ መንግሥት ተቀበለ

Date:

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ጨምሮ ሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ሀገር እንዲገቡ ከቅዱስ ሲኖዶስ የቀረበውን ጥያቄ መቀበሉን መንግሥት አሳወቀ።

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ መንግሥትን እንዲያናግሩ በወከላቸው ብፁዓን አባቶች አማካኝነት ከመንግሥት ጋር ተነጋግረው በተደረገው ስምምነት መሠረት ሦስት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ መፈቀዱን ገልጿል።

መንግሥት የቀረበውን ጥያቄ እንደተቀበለ አስታውሶ ችግሮች እንዲፈቱ ተቀራርቦ መነጋገር ከሁሉም ተሻለ መፍትሔ መንገድ እንደሆነም በመግለጫው አመላክቷል።

በዚህም መሠረት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ(ዶ/ር) የኒዎርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፣ ብፁዕ አቡነ ያእቆብ የጆርጅያና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ (ዶ/ር) የሰሜን ካሊፎርኒያ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በግንቦት 6/2017 ዓ/ም ለሚጀምረው የዚህ ዓመት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንዲገኙ መንግሥት የሚጠበቀውን ሁሉ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በተፈጠረው ችግር ምክንያት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ከጥር 28/2016 ዓ/ም ጀምሮ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ያዕቆብና ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ(ዶ/ር) ደግሞ ከግንቦቱ 2016 ዓ/ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ተገኝተው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤያትን እንዳልተሳተፉ የሚታወስ ነው።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ስለአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...