ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ እንዲቋቋም እገዛ ካደረገችበት የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) እንደሚያስወጡ ዝተዋል። ፕሬዝዳንቱ ግን ይህንን ዓይነቱን ውሳኔ እንደሚያሳልፉ ሲነገሩ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በአውሮፓውያኑ 2017 ለመጀሪያ ጊዜ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸውንም በፊት በተደጋጋሚ ኔቶን “የወረቀት ላይ ነብር” በማለት ያጣጥሉት ነበር። “ያረጀ” ሲሉ የሚጠሩት ይህ ጥምረት የአሜሪካን “ሀብት እያስወጣ” መሆኑንም ይናገሩ ነበር።
በ2019 ደግሞ “በዚህ ዛቻቸው ላይ ወደ እርምጃ ለመግባት እየተዘጋጁ” መሆኑን የሚያሳይ “ግልጽ ምልክት” አሳይተው እንደነበር የቀድሞው የኔቶ ዋጋ ፀሐፊ የንስ ስቶልተንበርግ በሳተሙት መጽሐፍ ላይ ከትበዋል።
የጥምረቱን ወታደራዊ ወጪ ሲተቹ የቆዩት ትራምፕ፤ አገራት ከጥቅል የአገር ውስጥ ምርታቸው ውስጥ ሁለት በመቶውን መከላከያ ላይ ማዋል እንዳለባቸው በሚያዝዘው በአውሮፓውያኑ 2014 የወጣ የኔቶ “መመሪያ” ደስተኛ እንዳልሆኑም ገልጸዋል።
ይህ መመሪያ ከወጣ በኋላ ሁሉም አባል አገራት በሚባል ደረጃ ወታደራዊ አቅማቸው ላይ የሚያውሉትን በጀት ጨምረዋል። ከፊሉ ይህንን እርምጃ የወሰዱት በትራምፕ ዛቻ ምክንያት ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ከሩሲያ በኩል እየጨመረ በመጣው ስጋት የተነሳ እንደሆነ የቢቢሲ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዋና ዘገቢ ሊስ ዱሴት ትገልጻለች።
ኔቶን ለቅቆ የመውጣት ጉዳይ ግን በፕሬዝዳንቱ ብቻ የሚተላለፍ ውሳኔ አይደለም። ፕሬዝዳንቱ የሴኔቱን ሁለት ሦስተኛ ድምጽ ሳያገኙ ወይም በኮንግረስ ሕግ ሳይጸድቅ በተናጠል ከኔቶ መውጣት አይችሉም።
ይህንን አሠራር የዘረጋው ሕግ በ2024 ሲጸድቅ ድጋፍ ከሰጡት አንዱ አሁን የኢራንን ጦርነት የሚደግፉት የትራምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ናቸው።
ሩቢዮ ማክሰኞ ዕለት ፎክስ ኒውስ ላይ ቀርበው አሜሪካ የጥምረቱ አባል መሆኗ “አሁንም ለዓላማዋ እየጠቀመ” መሆን እና አለመሆኑን “መልሶ እንደሚመረምር” ተናግረዋል። ሩቢዮ አክለውም ኔቶን “አሜሪካ አውሮፓን ለመደገፍ እንዲሁ የተቀመጠችበት” ጥምረት ነው ሲሉ ገልጸውታል።
በአውሮፓውያኑ 2026 መጀመሪያ ላይ ትራምፕ አሜሪካ ኔቶ እርምጃ እንዲወስድ ባታደርግ ኖሮ ሩሲያ ዩክሬንን ሙሉ በሙሉ ትቆጣጠር ነበር ብለዋል።
በአውሮፓውያኑ 2011 አሜሪካ ላይ የ9/11 ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ ኔቶ በአንቀጽ 5 መሠረት ለአሜሪካ መጠነ ሰፊ ድጋፍ አድርጓል። ይህ አንቀጽ በአንድ አባል አገር ላይ የሚሰነዘር ጥቃት በሁሉም ላይ እንደተሰነዘረ ጥቃት እንደሚቆጠር ይደነግጋል። በዚህም የኔቶ ወታደራዊ አቅም በአንቀጽ 5 መሠረት ጥቅም ላይ ሲል ለመጀመሪያ ጊዜ
