ትራምፕ የጄፍሪ ኤፕስቴይን ሰነዶች ይፋ እንዲሆኑ ጠየቁ

Date:

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ታዳጊዎችን በወሲብንግድ በማሰማራት የተፈረደበት ጄፍሪ ኤፕስቴይንን ሰነዶች ይፋ እንዲያደርጉ ጠየቁ።

ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት “ምንም የምንደብቀው ነገር ስለሌለ”ሰነዱን ይፋ ማድረግ አለባቸው ብለዋል።

ትራምፕ ከዚህ ቀደም  ሰነዱ እንዳይለቀቅ ሲሟገቱ የቆዩ ሲሆን፥ አሁን ላይ ምክር ቤቱ በዚህ ሳምንት በጉዳዩ ላይ ስብሰባ አካሂዳለሁ ማለቱን ተከትሎ የሰነዱን ይፋ መሆን መደገፋቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

በስብሰባው ምክር ቤቱ የአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር የግለሰቡን ሰነዶችይፋ እንዲያደርግ አስገዳጅ ድምፅ ይሰጣል ነው የተባለው።

ታዋቂ የቢዝነስና የፖለቲካ ሰዎች ከግለሰቡ ጋር ግንኙነት አላችሁበሚል በበርካታ መገናኛ ዘዴዎች ጭምጭምታዎች ሲደመጡ ቆይተዋል።

እስካሁን ለጭምጭምታዎች በቂ ማስረጃ ያልተገኘ ሲሆን፥ በታዳጊዎችየወሲብ ንግድ የሚጠረጠረው ኤፕስቴይንም በፈረንጆቹ 2019 በማረሚያ ቤትህይወቶ አልፎ መገኘቱን ዘገባው አስታውሷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...

ሕወሓት ድብረጺዮንን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ

የክልሉ ፕሬዚዳንት ተደርገው የተመረጡት  ድብርጺዮን ገ/ ሚካዔል (ዶ/ር)  ቃለ...

” ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ” – ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ...

የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም

የጥንት ኢትዮጵያዊያንአርበኞች ድል 85 ኛው ዓመት መታሰቢያ ሚያዚያ...