የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበር መልቀቂያ በማስገባታቸው የአመራር ለውጥ ማድረጉን ፓርቲው አስታወቀ

Date:

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበር አሉላ ኃይሉ ነጋ በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ ከፍተኛ የአመራር ለውጥ መገረጉ ተገልጿል።

ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፤ በምክትል ሊቀመንበርነት እና በሊቀመንበርነት ድርጅቱን ለስድስት ዓመታት የመሩት አሉላ፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተካሄደው አጠቃላይ የአመራር ስብሰባ ላይ መልቀቂያቸውን አቅርበዋል ሲል ገልጿል።

አቶ አሉላ መልቀቂያ ማቅረባቸውን ለአዲስ_ስታንዳርድ አረጋግጠዋል።

አቶ አሉላ፣ “አሁን ለተጨማሪ ትግል መዘጋጀት አለብኝ፤ በትግራይ ውስጥ ኃላፊነትን በፈቃደኝነት መልቀቅ እንደ መደበኛ ነገር መታየት እና በፓርቲያችንና በትግራይ ፖለቲካ ውስጥ ባህል እንደሚሆን አምናለሁ” ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው (ፌስቡክ) ላይ አስፍረዋል።

“ሥልጣን የሥራ ቦታ ነው። ሥራ ደግሞ አድካሚ ነው፣ ስለዚህ ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ተገቢ ነው” በማለት አክለዋል።

ፓርቲው ባወጣው መግለጫ የአሉላን መልቀቂያ መቀበሉን እና “ክንፈ ሓዱሽን አዲሱ የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል” ብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...