የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ዋና አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር ቡድኑ ባሳየው እንቅስቃሴ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሩዋንዳን 2ለ0 እንዲያሸንፍ የመሩት አሜሪካዊው አሰልጣኝ ” በዝግጅት ወቅት የሰራነውን ስራ ሜዳ ላይ ተመልክቻለሁ። በእዚህ እድሜያቸው ባሳዩት ብስለት ደስተኛ ነኝ።” ሲሉ ገልፀዋል።
ከሁለት ግብ በላይ የማስቆጠር አቅሙ እንደነበራቸው የገለፁት ቤንጃሚን ዚመር በቀጣይ ጨዋታ ክፍተቶቻቸውን አርመው እንደሚመጡ ጠቅሰዋል።
