ቶምቦላን ጨምሮ በሚደረጉ የዕድል ሙከራ ግብር ወደ 20% ከፍ አለ

Date:

በኢትዮጵያ የዕድል ሙከራ ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ ገቢ የሚያገኙ ሰዎች ከሚያገኙት ጠቅላላ ገቢ ላይ የሚከፍሉት የገቢ ግብር መጠን ወደ 20% (ሃያ በመቶ) ከፍ ማለቱን አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ላይ ካፒታል ተመላክቷል።

ይህ ጭማሪ ቀደም ሲል በ2008 ዓ.ም. በወጣው የገቢ ግብር አዋጅ ከተደነገገው 15% የግብር ምጣኔ የጨመረ ነው።

በተሻሻለው አዋጅ መሰረት፣ በዕድል ሙከራ አሸናፊነት የተገኘው ገቢ ሲሰላ፣ ገቢውን ያገኘው ሰው ዕድሉን ለማግኘት ያወጣው ወይም የደረሰበት ማንኛውም ኪሳራ ከታክስ የሚቀነስ አይሆንም። ይህ ማለት አሸናፊዎች የሚያገኙት ጠቅላላ ገቢ ምንም አይነት ቅናሽ ሳይደረግበት ለግብር ተገዢ ይሆናል ማለት ነው።

“የዕድል ሙከራ” ተብሎ ሲገለጽ፣ የጨዋታው ውጤት በተሳታፊው ችሎታ ላይ ሳይሆን በዋነኝነት በዕድል ላይ የተመሰረተ ጨዋታን ያመለክታል። ይህ ትርጉም ሎተሪንና ቶምቦላን የመሳሰሉ የዕድል ጨዋታዎችን ያካትታል።

ይህ አዲሱ የግብር ምጣኔ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄዱ የዕድል ሙከራ ጨዋታዎች ላይ ለሚሳተፉ እና ገቢ ለሚያገኙ ሁሉ ተፈጻሚ ይሆናል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኔታንያሁ እና ትራምፕ የፊታችን ማክሰኞ በዋይት ሀውስ እንደሚወያዩ ተገለጸ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፤ ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ...

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ለማጠናከር ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ውይይት አካሄደች

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን...

የካፍ ፕሬዝዳንት የ2027 አፍሪካ ዋንጫ በ24 ተሳታፊ ሀገራት እንደሚካሄድ አስታወቁ

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሙትሰፔ የ2027...

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና መስጠት ጀመረ

ሆስፒታሉ በቀን ከ300 በላይ ታካሚዎችን ያስተናግዳል የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ...