ናይሮቢ ውስጥ የጦማሪው አልበርት ኦጅዋንግን ሞት ተከትሎ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ

Date:

የ31 ዓመቱ መምህርና ጦማሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያለ መሞቱን ተከትሎ በዛሬው ዕለት በናይሮቢ ማዕከላዊ የንግድ አካባቢዎች ተቃውሞዎች ተቀስቅሰዋል።

⛓️ ተቃዋሚዎች የፖሊስ ምክትል ኢንስፔክተር ጄኔራል ኤሊዩድ ላጋት ለኦጅዋንግ ሞት ምክንያት ናቸው በማለት እንዲታሰሩና ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል፡፡ ላጋት ከሥልጣናቸው ቢነሱም ብዙዎች ይህ እርምጃ በቂ አይደለም እያሉ ነው።

የቅድሚያ የፖሊስ ሪፖርቶች ኦጅዋንግ በእስር ቤት ውስጥ ጭንቅላቱ ከግድግዳ ጋር ከተጋጨ በሗላ እንደወደቀ ቢገልጹም፤ የመንግሥት የአስከሬን ምርመራ የኃይል ምት፣ የአንገት መታነቅና በርካታ ጉዳቶች እንደደረሱበት አሳይቷል።

📹 በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጩ ያሉ ምሥሎች ያልታወቁ ግለሰቦች ሰልፉን ለማደናቀፍ ሲሞክሩ ያሳያል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...