የአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት የውጪ ሃገር ዜጎች ዲቪን ጨምሮ ወደ አሜሪካ ሄደው በቋሚነት መኖር ሲፈልጉ የሚሰጣቸው ቪዛ ( Immigrant Visa) ሂደት በ75 ሃገራት ሊያቋርጥ ነው።
ፎክስ ኒውስ የስቴት ዲፓርትመንትን የውስጥ ማስታወሻ ተመለከትኩ ብሎ ባወጣው መረጃ፣ ማቋረጡ በፈረንጆቹ ጥር 21፣ 2026 ጀምሮ ወደ ስራ ይገባል።
ሂደቱ ይቋረጥባቸዋል ከተባሉ ሃገራት መካከልም ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ኤርትራ፣ሩሲያ፣ ብራዚል፣ፓኪስታን፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ታይላንድ ይገኙበታል።
የስቴት ዲፓርትመንት ውሳኔ በመንግስት ድጋፍ ላይ ጥገኛ የሚሆኑ የውጪ ሃገር ሰዎችን ለመቀነስ ነው ሲባል ባለፈው ህዳር የቪዛ ኦፊሰሮች የአመልካቾችን ጤና፣ የቋንቋ ክህሎት፣ ፋይናንስና የተለያዩ መመዘኛዎችን በመመልከት በመንግስት ድጋፍ ለመኖር የሚፈልጉ አይነት ከሆነ ቪዛ እንዲከለክሏቸው ታዘው ነበር።
የስቴት ዲፓርትመንት ቃለ አቀባይ ቶሚ ፒጎት የ75ቱ ሃገራት የቪዛ ሂደት ስቴት ዲፓርትመንት የመንግስትን ድጋፍ የሚጠቀሙ የውጪ ዜጎች እንዳይገቡ ለመከላከል እንዲቻል የቪዛ ሂደቱ እስኪገመገም እንደሚቆም አረጋግጠዋል።
በቅርቡ ዶናልድ ትራምፕ ከመንግስት ድጋፍ በመቀበል የሚኖሩ የውጪ ሃገር ሰዎችን ቁጥር ይፋ ሲያደርጉ
በአሜሪካ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ተወላጅ ስደተኞች መካከል 47.6% ያህሉ ቢያንስ ከቤተሰብ አንዱ የመንግስት ድጋፍ ተጠቃሚ እንደሆኑ መግለጻቸው ይታወሳል።
የቪዛ ሂደቱ በስቴት ዲፓርትመንት እስኪገለጽ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያልም ተብሏል።
@tikvahethmagazine
