አሜሪካ ኤርትራ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ልታነሳ ነው !

Date:


የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ አሜሪካ ከኤርትራ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል መንገዶችን እያሰላ መሆኑ ተሠማ። የፕሬዝዳንቱ አስተዳደር የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ማሱድ ቡሎስ፣ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር አሜሪካ በኤርትራ ላይ የጣለቻቸውን የተወሠኑ ማዕቀቦች የማንሳት ሂደት ለመጀመር ፍላጎት እንዳለው ለውጭ ዲፕሎማቶች መናገራቸውን ከባለሥልጣናት መስማቱን ጠቅሶ ዎል ስትሪት ጆርናል ዘግቧል።

ሌሎች ባለሥልጣናት በበኩላቸው፣ አሜሪካ ከኤርትራ ጋር ግንኙነቷን ለማሻሻልና ማዕቀቦችን ለማንሳት የያዘችው እቅድ በግምገማ ሂደት ላይ መሆኑን መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ኤርትራ በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር ሥር ከአሜሪካ ጋር ግንኙነቷን ለማሻሻል ፍላጎት እንዳላት በተደጋጋሚ ሲገልጡ ቆይተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...