ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ኅብረት የሰው ሠራሽ አስተውህሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ ሆነው ተሾሙ

Date:



ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአኅጉር ደረጃ ዘርፉን እንዲመሩ የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ሹመቱን እንደሰጣቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ በዘርፉ እያሳየች ያለው ተሞክሮ እውቅና ማግኘቱ፣ በሀገሪቱ የተቋቋመው የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ኢንስቲትዩት እና የተቀረጸው ብሔራዊ ስትራቴጂ ውጤታማነት ተመራጭ እንዳደረጋቸው ፅ/ቤታቸው የሹመት ደብዳቤውን ጠቅሶ ገልጿል፡፡

አኅጉራዊው ሹመት ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ነፃነት እና በክህሎት ልማት የምታደርገውን እንቅስቃሴ ለአፍሪካ አህጉር ተሞክሮ እንዲሆን ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርም ተመላክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው የካቲት ወር የኅብረቱ የሰው ሠራሽ አስተውህሎትና ዲጂታል ጤና አምባሳደር ሆነው መሾማችው ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...